የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ መሆኑ ተገለጸ

 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ መሆኑ ተገለጸ

 

 

     የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህገ- መንግሥታዊ ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ እጅግ የላቀ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ገለፁ።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ይህን የገለጹት የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ.ም በታላቁ ቤተ መንግሥት ለተሿሚ ጄኔራል መኮንኖች ማዕረግ ካለበሱና የምስክር ወረቀት ከሰጡ በኋላ ባሰሙት የመመሪያ ንግግር ነው።

እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለፃ፤ ሀገራችን የተያያዘችው የዕድገትና የልማት ጉዞ የበለጠ እንዲጠናከር ሠራዊቱ ህገ- መንግሥታዊ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት በመወጣት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ  በአድናቆት የሚታይ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የህዝቦችን ሉዓላዊነት በማስከበር ሠላምን በማረጋገጥ፣ እንዲሁም በሠላም ማስከበር ተልዕኮ  አኩሪ ተግባር በመፈጸም መላው ህዝብን ያኮራ እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ባሰሙት ንግግር፤ የተቋሙ ዝግጁነትና የግዳጅ አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።

የሠራዊቱ ግዳጅ በሀገር ውስጥ የውጭ ወረራን የመግታት፣ እንዲሁም ፀረ- ሠላምና ፀረ- ልማት ኃይሎችን በመከላከል የሠላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደቱ በስኬት እንዲቀጥል ሠላማዊ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሚገኝ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ተናግረዋል።

የሠራዊቱ ግዳጅ እየተጠናከረና እያደገ በመምጣቱ በብቃት ለመፈጸም የሚያስችል አደረጃጀትና የአመራር አቅም ግንባታ አስፈልጓል።  ይህንን መሠረት ያደረገ የማዕረግ እድገት መፈቀዱንም ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ አስታውቀዋል።

 

 

መንግሥት ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ  የሀገራችን ሠላም እንዲጠናከርና የህዝባችን ህገ- መንግሥታዊ መብቶች እንዲከበሩ የህግ የበላይነትን ለማስፈን የተቀናጀ  ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

 

ይህን ያስታወቁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ኃላፊና የመከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ላይ የካቲት 10 ቀን 2010 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ክቡር ሚኒስትሩ በዚሁጋዜጣዊ መግለጫቸው የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች በአንድ ኮማንድ ሥር ተቀናጅተው የመንግሥትን ውሳኔ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ መታዘዛቸውን አስታውቀዋል።

መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎች የሀገርን ሠላምና ደህንነት፣ እንዲሁም የዜጎችን ህይወትና ንብረት ለመጠበቅ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ህዝቡ ከጎናቸው እንዲሆን፣ ወጣቶችም ለሠላም መጠናከር ዘብ እንዲቆሙ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

አዋጁ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ለ6ወራት እንደሚቆይና በ15 ቀናት ውስጥ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅም አስረድተዋል።

በሌላም በኩል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት አዋጁን ለመተግበር ባወጣው ዕቅድ ላይ ከፌዴራልና ከክልል ከፍተኛ የፀጥታ አካላት ጋር ውይይትም በማካሄድ ሥራ ጀምሯል።

የኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ኃላፊና የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፤ በተደረገው ውይይት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

እንደ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ገለፃ፤ ዋና የእቅዱ አካል ተብለው ውይይት የተካሄደባቸው የዜጎች ህገ- መንግሥታዊ መብቶች እንዳይገደቡ፣ የሽብርና የነውጥ ኃይሎችን የመቆጣጠርና በዚህ ተግባር የሚሳተፉ ወንጀለኞችን በህግ ቁጥጥር ሥር የማዋል፣ ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ፣ ህገ- ወጥ የሰውና የጦር መሣሪያ ዝውውርና ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር ኬላዎች ማጠናከር፣ ከህዝብ ጋር ውይይት በማድረግና የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥ ወደ ተረጋጋ ሠላማዊ ሁኔታ መመለስ ናቸው።

ሚኒስትር ሲራጅ በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫቸው የተለያዩ የህዝብ መድረኮችን በመጠቀም ከህዝቡ ጋር ውይይት እንደሚያደርግ፣ በሁከትና ብጥብጥ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ቀድሞ ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ ለማድረግ በዕቅዱ ይሰራል።

በሁከትና ብጥብጡ የወደሙ የመንግሥት ተቋሞችና ንብረቶች፣ የተዘረፉ የግለሰብ ንብረቶች ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የማስመለስና መልሶ የማቋቋም ሥራ እንደሚሰራ አቶ ሰራጅ አስረድተዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት እስከታች ያሉ የፀጥታ ኃይሎች በአንድ ኮማንድ ፖስት ሥር ሆነው በሀገሪቱ 8 ቀጣናዎች ዕቅዱን እንደሚተገበር የገለጹት አቶ ሲራጅ፤ በየቀጣናዎቹም የዕዝ አመራሮች መመደባቸውን አስታውቀዋል።

በውይይቱ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ መሰጠቱንና እያንዳንዱ ኮማንድ ፖስት የራሱን እቅድ ይዞ ወደ ተግባር እንደሚገባም አቶ ሲራጅ አስረድተዋል።

በውይይቱም መክፈቻ ላይ የአስቸኳይ ኮማንድ ፖስት ጊዜ ርምጃ አፈፃፀም መመሪያ 01/2010 መውጣቱ ተገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ ርምጃ አፈፃፀም መመሪያ ሁለት ክፍሎችና ሦስት ንፁሳን ክፍሎችን የያዘ ነው።

 

የሠራዊታችን አኩሪ ገድሎች በህዝቦቻችን ዘንድ ከፍተኛ ቦታ ይዘው ይኖራሉ

በፀጋዬ ገብሬ (መቶ አለቃ)                 ዜና ሀተታ

     የጋዜጣው ሪፖርተር

                                     ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት

 

በበጀት ዳይሬክቶሬት ሥልጠና ተሰጠ

በሰለሞን ጫኔ (መ/አለቃ)

የጋዜጣው ሪፖርተር

 

የኢፌዴሪ መከ ላከያ በጀት ዳይ ሬክቶሬት በበጀት አጠቃቀም ሥር ዓትና የበጀት ጥያቄ አካሄድ ላይ ሥልጠና ሰጠ።

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ መከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዮሃ ንስ ድንቃየው፤” ለተሳካና ውጤታማ ለሆነ የበጀት አጠቃቀም ሥርዓት የአመራሩ ሚና የጎላ ነው። አመራሩ ለሚፈጽመው ሥራ የሚሰጠውን በጀት በአግባቡና ሥርዓትን በጠበቀ መንገድ በመጠቀም ለታሰበለት ዓላማ ብቻ ማዋልና ጥያቄ የማያስነሳ ሥራ መስራት ይገባዋልም” ብለዋል።

በመኮንኖች ክበብ የተካሄደውን ሥልጠና የመሩት የመከላከያ በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ በበኩላቸው አመራሩ የተሳካ የሥራ ሂደት እንዲኖርና ብክነትን መከላከል የሚያስችል ሥራ መስራት እንደሚገባው ገልፀው፤ “የሥልጠናው ዋና ዓላማም ሁሉም የዕዝና የመምሪያ ኃላፊዎች ተመሳሳይ የሆነ የበጀት አጠቃቀም ዕውቀት በመያዝ ለቀጣይ ተቋሙ ለሚያደርገው የበጀት ድልድልና ልዩ ልዩ ሥራዎች በጋራ ለመስራት እንዲያስችል የታሰበ እንደሆነ ተናግረዋል”።

በተያያዘ ዜና፤ የበጀት ዳይሬክቶሬቱ ይህ ሥልጠና ከመስጠቱ ከሁለት ቀን በፊት በየክፍሉ ካሉት የበጀት ክፍል ኃላፊዎች ጋር የ6ወር አጠቃላይ የበጀት አጠቃቀም ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱን የመሩት የመከላከያ በጀት ዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ እንዳሉት፤  ሁሉም ክፍሎች አሁን በሚደረገው ውይይት የአንዱን ስህተት አንዱ እንዳይደግመው በማድረግና ለቀጣይ የግማሽ ዓመት አጠቃቀም ከአሁኑ በበለጠ መልኩ በስኬት ለማጠናቀቅ የሚጠቅምና ይህ ውይይት ለ2011 የበጀት ጥያቄና ድልድል እንደ መነሻ  የሚያገለግል ነው።

 

የሰው ኃይሉን በማልማት ዘርፈ- ብዙ ለውጦች መመዝገባቸው ተገለፀ

በበየነ በቀለ

 

 

የኢፌዴሪ መከላከያ የሰው ኃይሉን በማልማትና አቅሙን በማሳደግ ዘርፈ- ብዙ ለውጦችና እድገት ማስዝገቡን ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ይህን የገለፁት ባለፈው ሰሞን የከፍተኛ ባለሌላ ማዕ ረግተኞች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለ22ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ሠልጣኞች በመጋቢ %አለቅነት ማዕረግ ባስመረቀበት ወቅት ብልጫ ላመጡ ተመራቂዎች ሽልማት ከሰጡና ማዕረግ ካለበሱ በኋላ ባሰሙት ንግግር ነው።

የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኞች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለተቋሙ የሰው ኃይል ግንባታ ከፍተኛ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል ያሉት ጄኔራል ሰዓረ፣ መከላከያ በማንኛውም መስክ አቅሙን በማጠናከር ለተልዕኮው ራሱን በማዘጋጀት በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ግዳጅ ተጨባጭ ለውጦች እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ተመራቂዎች አሀዱን ለተልዕኮ  በብቃት በማዘጋጀት፣ በማሠልጠንና በመገንባት፣ ደስተኛና ዴሞክራሲያዊ ባህሪ የተላበሰ፣ ተግባብቶ መስራትና የመረዳዳት ባህሪ እንዲኖረው ጠንክረው መስራት እንዳለባቸውና ለተግባራዊነቱ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኞች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ብ/ጄኔራል  መንግሥቱ ተክሉ ባቀረቡት የሥልጠና ሪፖርት፤ በተሻሻለው የትምህርትና ሥልጠና ሂደት ሠልጣኙም ሆነ አሠልጣኙ ደስተኛ በመሆን ሥልጠናውን አጠናቋል። የተደረገውም የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ትክክለኛና ሳይንሳዊ መሆኑን ማረጋገጥ እንደተቻለ ገልፀዋል።

የሥልጠና ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ከሥልጠናው ጎን ለጎን በየትምህርት ዓይነቱ አሠልጣኞች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በመደረጉ የተፈለገውን ግብ በማሳካት አበረታችና ውጤታማ አፈፃፀም መመዝገብ እንደተቻለ ብ/ጄኔራል መንግሥቱ አስረድተዋል።

ተመራቂዎች በተቋሙ መመሪያና አሰራር የሚመሩ፣ ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ወቅትም አሀድን በመምራትና በመገንባት፣ የማስተዳደር ዕውቀትና ክህሎት ባለቤት መሆናቸውን በግልም ሆነ በቡድን በተደረገው ምዘና ማረጋገጥ መቻሉን የትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ አስታውቀዋል።

ለአራት ወራት ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድርም ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን፤ በስፖርታዊ  ውድድሮቹም አሸናፊዎች ከክብር እንግዳው የዋንጫ ሽልማት ተቀብለዋል።

 

ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ  ሠልጣኞች ን አስመረቀ

በሰለሞን ጫኔ (መ/አለቃ)

    የጋዜጣው ሪፖርተር

 

በኢፌዴሪ መከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና እና የበታች ሹም ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለ26ኛ ጊዜ ሠልጣኞችን አስመረቀ።

ሰሞኑን በማሠልጠኛ ማዕከሉ በተከናወነው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት በሥራ ጥራት ብልጫ ላመጡ አሰልጣኞችና ሠልጣኞች ሽልማት በመስጠት የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ክቡር ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ናቸው።

ኃላፊው በንግግራቸው ተቋሙ በየጊዜው በሚያደርገው ብቃት ያለው ሠራዊት ግንባታ ላይ ምልምል ወታደሮችን በማሠልጠን ወደ ነባሩ ሠራዊት ማዋሀድ አንዱ እንደሆነ ገልፀው፤ በዕለቱም የተመረቁ መሠረታዊ  ወታደሮች በትምህርት እና በልዩ ልዩ ሙያ ተመርቀው የተቀላቀሉ ስለሆነ ለተቋሙ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል። ቀጣይ በሚሄዱበት አሀድ በሥልጠና ያገኙትን አቅም በመያዝ ከነባሩ ሠራዊት ጋር በመሆን ሀገርና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በተሰማሩበት ሥራ ሁሉ በአግባቡ መወጣት አንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና እና የበታች ሹም ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ  ብርጋዲየር ጄኔራል ፍሰሀ በየነ በበኩላቸው፤ ሠልጣኞቹ ማሠልጠኛ ማዕከሉ ያስቀመጠውን የመመረቂያ መስፈርት በእውቀት፣ በችሎታ፣ በአስተሳሰብና በባህሪ አሟልተው ለምረቃ እንደበቁ ገልፀዋል። 

አዛዡ አያይዘውም፤ “ውትድርና  ቆራጥነት፣ ታታሪነትና ታማኝነት የሚጠይቅ ሥራ ስለሆነ  ተመራቂዎች በትምህርት የተሰጣችሁን ሥልጠና በመያዝ ቀጣይ በሚኖሩ ሥልጠናዎች እራሳችሁን በማብቃት ተቋሙን ማገልገል ይገባችኋል” ሲሉ አሳስበዋል።

 

ለታላቁ የኢትዮጵያ  የህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እደሚቀጥል ተገለፀ

የህዳሴውን ዋንጫ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ተረክቧል

በአስቻለው ኛኙኬ(መ/አለቃ)

    ከመከላከያ ሬዲዮ

 

 

የታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ  ግድብ ህዝባዊ ተሣትፎ ማስተባበሪያ ብሄራዊ ኮሚቴ በሁሉም ፀጥታ ሀይል ክፍሎች እዲዘዋወር ያዘጋጀው ዋንጫ የመጀመሪያውን ጉዞ ወደ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ባደረገበት ወቅት በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ በሠራዊቱ እና በአካባቢው ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

በዕዙ ጠቅላይ መምሪያ በተዘጋጀው የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ በክብር እግድነት የተገኙት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የመላው ህዝባችን አሻራ ያረፈበት ታላቁ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድባችን በወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኝ እና ሂደቱም ለደቂቃም እንዳይቋረጥ በማድረግ ረገድ የሠራዊቱ ሚና የላቀ መሆኑን ገልፀው “የክልላችን ህዝብና መንግስት ለህዳሴው ግድቡ እያበረከተ ከሚገኘው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ሠራዊቱ ተሣትፎ እና የማገዝ ሚናውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጽኑ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።”

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦ ፕሬሽናል ሜ/ጀኔራል በላይ ስዩም ዋንጫውን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት መላው የዕዙ አባላት የህዝባችንን ሉዓላዊነት በአስተማማኝ ከማረጋገጥ ዋነኛ ተልዕኮው ባሻገር በተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን የድርሻውን ሲያበረክት ቆይቷል። በተለይም የታላቁ የህዳሴ ግድባችን የመሠረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ለተከታታይ ዓመት ያልተቋረጠ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሆኑም አረጋግጠዋል።

የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ሜ/ ጄኔራል በላይ ስዩም በንግ ግራቸው አረጋግጠዋል።

ዋንጫውን ለዕዙ ያስረከቡት የመከላከያ ስነ-ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብ/ጄኔራል ሙላት ጀልዱ በበኩላቸው “ እኛ የሠራዊቱ አባላት ለሠላም፣ ለልማት እና ለዲሞክራሲ መጠናከር ከህዝባችን ጎን ተሠልፈን በምንፈፅመው ተግባር ህዝባዊ ሠራዊት መሆ ናችንን ማስመስከር ችለናል ብለዋል”።

 ብ/ ጄ ሙላት አክለው የዚሁ ማረጋገጫ የሆነውን የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ስትረከቡም መላው ዕዙ አባላት ባሉበት ሁሉ በማዘዋወር እስካሁን እየተደረገ ያለውን የተሣትፎና የድጋፍ ንቅናቄ የበለጠ አጠናክራችሁ ማስቀጠል ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳሰበዋል። 

 

በልዩ ልዩ የሠራዊት ክፍሎች ሠልጣኞች ተመረቁ

 

የማዕከላዊ ዕዝ ፋና ማሠልጠኛ ማዕከል በዕዙ ሥር ከሚገኙ ክፍለ ጦሮች የተውጣጡ የበታች ሹም ማዕረግተኞችን ለ7ኛ ጊዜ አሰልጥኖ አስመረቀ።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት በሥልጠና ቆይታቸው ብልጫ ላመጡ ሠልጣኞች የምስክር ወረቀት ሰጥተው ማዕረግ በማልበስ የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ  ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ በንግግራቸውም፤ የሠራዊቱን የግዳጅ አፈጻጸም ብቃት በዕውቀትና በችሎታ ላይ የተመሠረተ ሲሆን የበታች ሹም አመራሮች ከፍተኛውን ድርሻ ወስደው እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

“እያንዳንዱ  አመራር ግዳጁን በተቋሙ ደንብና መመሪያዎች መፈጸም ይገባዋል” ያሉት ምክትል አዛዡ፤ የሠራዊቱን የመፈጸምና የማድረግ አቅም ከፍ በማድረግ በራስ የመተማመን አቅምን ማዳበር እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የዘገበልን  የማሠልጠኛ ማዕከሉ ሪፖርተር %አለቃ ቢኒያም አንዳርጋቸው ነው።

በተያያዘ ዜና፤ የደቡብ ምሥራቅ ዕዝ ወታደራዊ ማሠልጠኛ በልዩ ልዩ ሙያ ያሰለጠናቸውን ወታደራዊ ሙያተኞች አስመርቋል። ተመራቂዎቹም በዕዝ ሥር ከሚገኙ ክፍለ ጦሮች የተውጣጡ ሲሆን  በመሃንዲስ፣ በመገናኛ፣ በዘመቻና በሴክሬታሪ  ሙያ የሰለጠኑ ናቸው።

በምረቃ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ምሥራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል  ብርጋዲየር ጄኔራል አማረ ገብሩ በመገኘት ብልጫ ላመጡ አሰልጣኝና ሠልጣኞች ሽልማት በመስጠት የሥራ መመሪያ ንግግር አድርገዋል።

ጄኔራል መኮንኑ፤ “ በማሠልጠኛ ማዕከሉ ቆይታችሁ ያገኛችሁትን ዕውቀት ህዝባዊና ህገ- መንግሥታዊ ተልዕኳችሁን በአግባቡ ለመፈጸም እንደሚያግዛችሁ እምነቴ ነው፤ ያገኛችሁትንም አቅም በማዳበር በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት በቁርጠኝነትና በታማኝነት ግዳጃችሁን መወጣት አለባችሁ” ሲሉ አሳስበዋል። ዘገባዎቹን ያደረሰን ሻምበል ባሻ ዳምጤ ማናዬ የዕዙ ሪፖርተር ነው።

 በሌላ ዜና በደጀን ክፍለ ጦር ከሁሉም ሬጅመንቶች ለተውጣጡ ከሻምበል እስከ ጓድ መሪ ላሉ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቋል።

በሥልጠናው ማጠቃላይ ላይ በመገኘት የምስክር ወረቀት በመስጠት የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት፤ የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመስክ ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራልበርሄ ኪዳኔ ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ በንግግራቸው፤ “ሥልጠና የአቅም ማጠናከሪያና የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት ስለሆነ ሠልጣኞች በሥልጠና ቆይታ ያገኛችሁትን አቅም በመጠቀም በአመራርነት ብቃት ተግባር ተኮር ሥራዎችን በመስራት በላቀ ውጤት መፈጸም  ይገባችኋል” ብለዋል።

የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አለሙ ተካ በበኩላቸው፤ በተሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሠረት ሠልጣኞች በማንኛውም ግዳጅ መመሪያና ደንብን መሠረት አድርገው በመስራት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል። የዘገበችው የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ም/ !አለቃ ሰናይት ሀ/የሱስ ነች።

በተመሳሳይ ዜና የማዕከላዊ ዕዝ 8ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ ባለሌላ ማዕረግተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቶ አስመረቀ።

በሥልጠናው ማጠቃላይ ላይም በመገኘት ለተሿሚዎች ማዕረግ ያለበሱትና የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የ8ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ያሲን መሀመድ ናቸው።

በንግግራቸው፤ ሠልጣኝ አመራሮች በሥልጠናው ያገኙትን አቅም በመጠቀም ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። ዜናውን ያደረሰን የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ሻለቃ መጋቢ ባሻ ባዩ ወርቅነህ ነው።

 

ለፋይናንስ ሙያተኞች ሥልጠና ተሰጠ

በሰለሞን ጫኔ (መ/አለቃ)

    የጋዜጣው ሪፖርተር

 

 

የመከላከያ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ለዕዝና ለመምሪያ  የፋይናንስ ሙያተኞች ለሦስት ቀን የቆየ ሥልጠና ሰጠ።

በሥልጠናው ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ መከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ እንዳሉት ሁሉም የፋይናንስ ሙያተኞች ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ የፋይናንስ ህጉን የተከተለ ሥራ በመስራትና ብክነትን በመከላከል ከተጠያቂነት የፀዳ ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ገልፀው፤ የፋይናንስ ዘርፍ ያለበትን የሰው ኃይል እጥረትና በቅንጅት የመሥራት ችግርን በቀጣይ ለመፍታት የረዥምና የአጭር ጊዜ ዕቅድ በማስቀመጥ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ኮሎኔል ፍፁም ገ/እግዚአብሄር በበኩላቸው፤ ፋይናንስ ዘርፍ አጠቃላይ የፌዴራል ክፍያ ሥርዓትን የተከተለ ሥራ በመስራትና በኦዲት፣ በኢንስፔክሽን የሂሳብ ሪፖርት ክፍያ እና የፔሮል ህትመትና ሥርጭት ግልጽ በሆነ መንገድ መፈጸም እንደሚገባ ገልፀው ፋይናንሱ ክፍያ ሲፈጽም ሰነዶችን በመመርመርና በማረጋገጥ ከተጠያቂነት ነፃ የሆነ ሥራ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። “ለሠራዊቱም ፈጣን የሆነ አገልግሎት መስጠት የሁሉም ኃላፊነት ነው” ብለዋል።

አንዳንድ ሠልጣኞች በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት ቀጣይ ለሚሰሩት የጋራ ሥራ ትልቅ አቅም እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።

 

 

ህዝባዊነቱን እያጎለበተ የህዳሴው ዋስትና የሆነ ሠራዊት

በፈይሣ ናኔቻ (ሻምበል)

የጋዜጣው ሪፖርተር             ዜና ትንታኔ

 

 

ስድስተኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በመላው ሀገራችን “ህዝባዊነታችንን እያጎለበትን ህገ-መንግሥታችንን በመጠበቅ የህዳሴያችን ዋስትና ሆነን እንቀጥላለን” በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

ከዝግጅቶቹ መካከል የህዳሴ ግድብ የሠላም ዋንጫ ርክክብና የመከላከያ ሠራዊት የፀጥታ ኃይሎች የሠላም ጉዞ፣ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት፣ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ የማጠቃለያ ዝግጅትና ህዝባዊ ድጋፎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በአዲስ አበባ የተካሄደው የሠላም ጉዞ መነሻውን ቴዎድሮስ አደባባይ በማድረግ መድረሻው መስቀል አደባባይ ሆኗል። “ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የሠላም ምንጭ ነው” በሚለው መርህም ጠንካራ መልዕክት ተላልፏል።

ሠራዊቱ የፌዴራልና የክልል ሠንደቅ ዓላማዎችን በማውለብለብ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስተማማኝ ዘብ በመሆን፣ ለዜጎች በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት ወደላቀ ደረጃ ያሸጋገረውን በእያንዳንዱ ዜጋ ላብ፣ ዕውቀትና አሻራ ያጎለበተውን ታላቁን ፕሮጀክት በዕውቀቱ፣ ጉልበቱና ገንዘቡም ለመደገፍ ዳግም ቃል ኪዳኑን አድሷል።

ሠራዊቱ ሽብርተኝነትን በትጋት እን ደሚከላከለው ሁሉ ለህዝባችን ቀንደኛ  ጠላት ሆኖ የቆየውን ድህነት በመዋጋትም ከህብረተሰቡ ጎን በመሰለፍ አጋርነቱን በማሳየት ላይ ይገኛል። አሁን ለስድስተኛ ጊዜ በተከበረው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀንም ገጽታውን በማጉላት ዕለቱን ዘክሯል።

ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ተሳትፎ ብሄራዊ ምክር ቤት ዋንጫውን የተረከቡት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሳ በዕለቱ ንግግር አድርገዋል። ሚኒስትሩ በንግግራቸው መከላከያ ሠራዊት ከህዝብ የወጣ፣ ለህዝብ የሚያገለግል እንደመሆኑ መጠን የህዝብ በሆነው ታላቁ ፕሮጀክት  ሀሩርና ቁር ሳይበግረው ሌት ተቀን በመጠበቅና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በቀጥታ በግንባታው በመሳተፍ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት፤ ሠራዊቱ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተካሄደው የሠላም ጉዞም ድጋፉን የበለጠ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ከህዝቡ ጋር በተደረገ ውይይትም ሠራዊቱን የሚመለከቱ በርካታ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በተለያዩ መድረኮች በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሠራዊቱን የሠላም አምባሳደርነት በማድነቅ ኩራት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

ሠራዊቱ በወታደራዊ ዕውቀትና ክህሎት ከዕለት ወደዕለት እያደገ መምጣቱን፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር በአብነት የሚጠቀስ የሀገሪቱ መፃኢ ተስፋና ዕድል አስተማማኝ ዋስትና መሆኑንና ሠላምን በመጠበቅ በማስፈን እያከናወነ የሚገኘውን ሰናይ ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳስበዋል። በህብረተሰብ ክፍሎች ትልቅ አጽንኦት የተሰጠው የሠራዊታችን የማይሸራረፍ ህዝባዊነት ነው።

የሁሉንም ህዝቦች ባህልና ወግ የሚያከብር    እንጂ የማይፈራ የሚተማመኑበት ቃሉን የማያጥፍ ታማኝ ሠራዊት መሆኑን የውይይቶቹ ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የመስተዳድር አካላትም ሠራዊቱ ያከናወናቸው ተግባራት ለሁሉም የሥራ መስኮች አርአያ መሆን የሚችል ልንማርበት የሚገባ ማንነት ባለቤት ነው ብለዋል።

በሠራዊት ቀን አከባበር የተቀመጡ ዓላማዎች ግባቸውን የመቱ ሲሆን ዕለቱን ምክንያት በማድረግ የተለመደውን የሠ  ራዊቱን ባህል የሚያንፀባርቁ ህዝባዊ ድጋፎች ተደርገዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው አቅመ ደካሞች፣ ወላጆቻቸውን ያጡ  ችግረኛ ህፃናት እንዲሁም አካል ጉዳተኞች ከተደረገላቸው ድጋፍ በተጨማሪ ቀኑን የህዝብ ወዳጅ ከሆነው ሠራዊታችን ጋር አክብረዋል።

ሠራዊቱ በስፖርታዊ ውድድሮች ከህብረተሰቡ  ጋር የበለጠ ተቀራርቧል። ውስጣዊ አንድነቱን አጠናክሯል። በህዝባዊ መሠረት ላይ የተገነባውን የአሸናፊነት መንፈሱን ወደላቀ ደረጃ አሸጋግሯል።

ለፀጥታ ኃይሎች የተበረከተው የሠላም ዋንጫ በሚኒስትሩ አማካይነት ተቀብሎ በሠራዊቱ ክፍሎች ማዘዋወር የጀመረው ጀግናው የህዝብ ልጅ በህዝብ ልብ ያገዘፈውን የልማት ኃይልነቱን ዳግም በማረጋገጥ ወደ ሌሎች ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

 

ክፍለ ጦሩ ሠልጣኞችን አስመረቀ

      አንገሶም  አስፋው(!አለቃ)

የቴሌቪዥን ሪፖርተር

በመሃንዲስ ዋና መምሪያ የተዋጊ መሃንዲስ ክፍለ ጦር በፈንጂ አጠማመድና አወጋገድ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ሙያተኞች አስመረቀ።

በምረቃ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ሙሉ ግርማይ ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ በሥልጠናው ሂደት ብልጫ ላመጡ ሠልጣኞችና ጥሩ የሥራ አፈፃፀም ለነበራቸው አሠልጣኞች ሽልማትና የምስክር ወረቀት ካበረከቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ የፈንጂ ማምከን ሙያ ግዳጅን በተሳካ ሁኔታ መፈጸም የሚያስችል ቁልፍ ተግባርና ክቡር ሙያ ነው ብለዋል። “በዚህ ሙያ ሠልጥናችሁ 6ኛውን የሠራዊት ቀን በምናከብርበት ዕለት በመመረቃችሁ ድርብርብ ኃላፊነቶችን በመያዝ ህዝብና መንግሥት የጣሉብንን አደራ በላቀ ብቃት ለመፈጸም የሚያነሳሳ ነው” ያሉት ጄኔራሉ ቀጣይም በምትሄዱበት በትምህርትና ሥልጠና አሀድ በየዕለቱ እራሳችሁን ማብቃት ይኖርባችኋል ብለዋል።

የተዋጊ መሃንዲስ ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋ ዲየር ጄኔራል ሰመረ ገብረእግዚአብሄር በበኩላቸው፤ ክፍለ ጦሩ ከተቋሙ የሚሰጠውን የሰው ኃይል በሙያ አብቅቶ ወደ ሁሉም የግዳጅ ቀጣና በማሰማራት ተቋሙ የሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ እየተወጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

አንዳንድ ሠልጣኞች በሰጡት ተመ ሳሳይ አስተያየት በሥልጠናው ወቅት ለቀጣይ ግዳጃቸው የሚያበቃ  ጥሩ አቅም የፈጠረላቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!