ዳግም ቃላችንን የምናድስበት ቀን

ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ በህይወት ከተለዩን አምስት ዓመት ሞላ። እኚህ ታላቅ መሪ በህይወት ዘመናቸው አስረክበውን የሄዱት አሻራዎች ሀገራችንን ከድህነት በማላቀቅና የህዝባችንን መፃዒ  ዕድል በማለምለም ያስገኘው ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ ነው።

 

በህይወት ዘመናቸው የቀየሷቸው ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ሀገራችን ከድህነት አዘቅት ውስጥ አውጥቶ ባለራዕይ እንድትሆን ያስቻለ ነው። ሀገራችን ትታወቅበት ከነበረው የጦርነት፣ የረሃብና የኋላቀርነትና የፀረ - ዴሞክራሲ ታሪክ በመቀየር ፈጣን የኤኮኖሚ ዕድገት የሚመዘገብባት፣ ህዝባችንም ሠላምንና ዴሞክራሲን የሚያጣጥምበት ሀገር እንድትሆን አስችለዋል።

 

እንዲሁም የሀገራችን መጻዒ ዕድል ብሩህ እንዲሆን በህይወት ዘመናቸው ደክመዋል። በዚህ ፋታ የሌለው ትግላቸውም ሀገራችን በመልማት ላይ ካሉ ሀገሮች ተርታ እንድትሰለፍና የዓለም አቀፉንም ማህበረሰብ ትኩረት እንድታገኝ አስችለዋል።

 

ድህነት ዋነኛው ጠላታችን ነው በሚል ጽኑ አቋምም መላው ህዝባችን በድህነት ላይ እንዲረባረብ በማድረግ የሚሊዮኖች ህይወት እንዲቀየር አድርገዋል። በበሳል አመራራቸው በሀገሪቱ ታሪክ ታይተው የማይታወቁ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተነድፈው ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ ሚናቸው እጅግ ከፍተኛ ነው።

 

በተለይም የሀገራችን የፀረ-ድህነት ትግል ያለምንም እንቅፋት እንዲቀጥል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሚመራበትን ዶክትሪን በመቅረጽ፣ የተቀረፀውንም ወታደራዊ ጥበብ እንዲላበስ በማድረግም ለህገ - መንግስቱና ለህገ -መንግስታዊ ሥርዓቱ አስተማማኝ ዘብ እንዲሆን በጠንካራ የመከላከያ ሠራዊት ግንባታም ያሳረፉት ተቋማዊ አሻራ ጎልቶ የሚታይ ነው።

 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የህገ -መንግስቱ የሠላም ዋስትና በመሆንም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ  ሀገር የሚሰጠውን ማናቸውንም ግዳጆች በእምነትና በጀግንነት እየፈጸመ ይገኛል። ጠላቶቹንም በጽናት ተፋልሞ ድልን ደጋግሞ በመቀዳጀት አስተማማኝ ኃይል እንዲሆን በማስቻል የታላቁ መሪ ሚና ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

 

እኛ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የታላቁን መሪ 5ኛ ዓመት ስንዘክር በታላቅ አደራ አስረክበውን የሄዱትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ከህዝባችን ጋር በመሆን የታለመላቸውን ግብ እንዲያሳኩ ማድረግ፣ ሀገራችንም በልማት ጎዳና እያደረገች ያለውን ግስጋሴ ያለምንም እንቅፋት እንዲቀጥል ማስቻል ይገባል። ስለዚህ በታላቁ መሪ አርቆ አስተዋይነት በተቀረጸልን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ እየተመራን ከዘመኑ ጋር እየዘመንን አስተማማኝ የሠላም ኃይል እንደምንሆን ዳግም ቃላችንን ማደስ ይኖርብናል።

በብዛት የተነበቡ በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና...
ነሐሴ 26 12 2012 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ነሐሴ 17 12 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ ፣ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል...
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፤ የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር...