ሰራዊታችንና የልማት ተሳትፎ

በአከባቢ ስነ-ምህዳር ጥበቃና ልዩ ልዩ ያበረከታቸው ድጋፎች

      የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ህዝባዊ ወገንተኝነቱ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ግዳጅ በተሰማራባቸው አከበቢዎች ከአከባቢ መስተዳድርና ህዝብ በመገናኘት በእውቀቱ፤ በገንዘቡ፤ በጉልበቱ በማናቸውም የልማት ዘርፎች ግምባር ቀደም ሆኖ በመሰለፍ ሚናው እየተወጣ  ይገኛል፡፡ ከፈፀማቸው አኩሪ ተግባሮች ውስጥ በሙሉ ፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ከደመወዙ በማዋጣት ልማትን እየደገፈ ይገኛል፡፡ በተሰማራባቸው አከባቢዎች ጊዜውንና ጉልበቱን መስዋእት በማድረግ ለአቅመ ደካማ አባዎራዎችና እማዎራዎች ከእለት ጉርሱ ቀነሶ ከመስጠት ባሻገር፤ ማሳቸውን አርሶ ዘር በመዝራት፤ በማረም፤በማጨድና በመሰብሰብ ህዝባዊ አጋርነቱን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ እንዲሁም በመንገድ ስራ ላይ በንቃት መሳተፍ፤ትምህርትቤቶችና ጤና ኬላዎችን በገንዘቡና በጉልበቱ ከአከባቢ ህ/ሰብ በመሆን በመገንባትና የውስጥ ቁሳቁስ እንዲማላ በማድረግ፤የአከባቢ ስነምህዳር ለመጠበቅ ችግኞችን በመትከልና አንድ ኮዳ ውሀ ለአንድ ችግኝ በሚል መርህ ተገቢውን ክትትል በማከናወን፤ በእርከንና በውሀ መገደብ ስራ በመሳተፍ እንደ ዜጋ ከህዝብ ጋር በመሆን አኩሪ ተግባርን ከአመት ወደ አመት ያለማቋረጥ እየፈፀመ መጥተዋል፡፡  ከዚህ በተጨማሪም ወላጆቻቸውን በተለያየ ምክንያት በሞት ያጡ ህፃናት በአንድ አከባቢ በመሰብሰብ ሙሉ ወጪአቸውን በመሸፈን ትምህርት እንዲማሩ በማድረግና እንዲሁም በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ወቅትም ሰራዊታችን ቀድሞ በመድረስ የሰው ህይወት ታድገዋል፤የንብረት ውድመትም ተከላክለዋል፡፡        

     ሰራዊታችን ይህንን በጎ ተግባሩን  በ2009 ዓ/ም በተሰማራባቸው አከባቢዎች ከአከባቢው መስተዳድርና ህዝብ ጋር በመግባባት በገንዘቡ፤በጉልበቱ፤በእውቀቱ በበርካታ ድህነትንና ኃላቀርነትን ሊቀርፉ በሚችሉ የልማት አውታሮች እየተሳተፈ የመጣ ቢሆንም ከተሳተፈባቸው በጥቂቱ ለመግለፅ ያህል 1.933.416  ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ፤23.272 ሜትር በእርከን ስራ በመሳተፍ የአከባቢ ስነ ምህዳር ለመጠበቅ ተሳትፎውን አረጋግጠዋል አሁንም በማረጋገጥ ይገኛል፡፡ 8.085 ሄክታር አረም በማረምና ሰብል በመሰብሰብ ከ874 በላይአቅመ ደካማ የሆኑ አባወራዎችና እማወራዎች ችግራቸውን የማቃለል ስራ በመስራት  ህዝባዊ ወገንተኝነቱን አስመስክረዋል አሁንም በጎ ተግባሩን እየቀጠለ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ከራስ በፊት ለህዝብና ለሃገር የሚል እሴት በተግባር በማረጋገጥ ከእለት ጉርሱን በመቀነስ ድጋፍ እያደረገ ከመምጣቱ ባሻገር 64.875.762 ብር ከደመወዙ በፍቃደኝነት በማዋጣት የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለደረሰባቸው ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው የማህበረሰብ ከፍሎች የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ 192.360.130 ብር ደግሞ ለወላጅ አልባ ህፃናት አገልግሎት የሚውል ገንዘብ አበርክተዋል፡፡

በአጠቃላይ ሰራዊታችን የተሰጠውን ህገመንግስታዊ ተልእኮ ከሰላም ወዳድ ህዝባችን በመሆን የሃገራችን ህዳሴ ከፍታዋን ለማረጋገጥና ድህነትን ለመጨረሻ ግዜ ወደ መቃብሩ ለማስገባት እየተደረገው ያለው ትግል ግምባር ቀደምት በመሰለፍ አወንታዊ ሚናው በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ በመነሳት ሰራዊታችን በየትኛው አከባቢ ለግዳጅ በተቀሳቀሰባቸው አከባቢዎች በሙሉ የሰላምና የልማት ሃይል መሆኑን በመንግስትና በህዝብ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር ምስጋና እየተቸረው ይገኛል፡፡

ሰራዊታችን ለታለቁ ህዳሴ ግድብ ያደረገው ተሳትፎ

   መላው የኢትዮጱያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአንድ አሰባስቦ አንድ ቋንቋእንዲናገሩ ያደረገና ከትውልድ ወደ ተውልድ የሚሸጋገር አሻራቸውን ያስቀመጡበት ታላቁ ህዳሴ ግድብ በታለመለት ጊዜ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቅ እንዲችል ሰራዊታችን ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የተጠናከረ ጥበቃ ከመከናወን ባሻገር ግንባታው ለማፋጠን  በተደረገው ህዝባዊ ተሳትፎ ከመጀመሪያ ጀምሮ አስከ አሁን ድረስ በራሱና በቤተሰቡ ጭምር ቦንድ በልዩ ሁኔታ በመግዛት፤እንደማንኛውም መንግስት ሰራተኛ ከደመወዙ ቦንድ በመግዛት፤ ለህዳሴ ግድብ ማጠናከሪያ የሚውል የተዘጋጀው ቶምቦላ ሎተሪ እና ትሸርት ለራሱና ለቤተሰቡ በመግዛት እንዲሁም ታለቁ ህዳሴ ግድብ አሁን ለደረሰው የማመንጨት አቅም ከፍ እንዲይል የሰራዊታችን እንጅነሮች የተጫወቱት ሚና በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ሰራዊታችንና በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ሲቪል ሰራተኞች ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለማቋረጥ ከወር ደመወዛቸው ቦንድ በመግዛትና በጥሬ ገንዘብ በስጦታ መልክ በማበርከት በጠቅላላ ከ810ሚልዮን ብር ገቢ አድርገዋል፡፡ አሁንም ድጋፋቸውን በመቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡ በየዓመቱ የተሰበሰበውን ገንዘብ ሲተነተን በ1ኛ ዙር 146.025.977.79 ብር በ2ኛ ዙር 149.645.071.65 ብር በ3ኛ ዙር 135.065.549.48 ብር በ4ኛ ዙር189.786.461.77 ብር በ5ኛ ዙር 189.265.727.85 ብር ጠቅላላ ድምር 809. 788. 788. 54 ብር ሲሆን በስጦታ የተበረከተ ገንዘብ 395.666.43 ብር በአጠቃለይ ከ01/ 11 /23 ዓ/ም እስከ 30/ 10/2009 ዓ/ም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል  በመከላከያ ሰራዊታችንና በሲቪል ሰራቶኞቻችን ተሰብስቦ ገቢ የሆነ ገንዘብ  810.184.454.97 ብር ነው፡፡ ይህ ገንዘብ የቲሸርትና የቶምበላ ግዢ እና በርካታ ልዩ ልዩ ድጋፎች ያደረጋቸው ተሳትፎ አይጨምርም፡፡

        በአጠቃላይ ሰራዊታችን ሃገራችን እየተከተለቺው ያለው ድህነትንና ኃላቀርነት በማጥፋት በአጭር ጊዜ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ለማሰለፍ የተጀመረው የህዳሴ ጉዞ በመደገፍ ያደረገውን አስተዋፅኦ በልማታዊ መንግስታችንና በመላው ህዝባችን በየግዘው አድናቆት እየተቸረው መጥተዋል፡፡  

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!