ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ሠራዊቱን ጎበኙ

የኢፌዴሪ መከላከያ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በሠራዊቱ የግዳጅ ቀጣና በመዘዋወር ጉብኝት አደረጉ።

በመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ በክቡር ሌተና ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም የተመራው የወታደራዊ አዛዦች  ልዑክ የሰሜን ምስራቅ ዕዝን ጎብኝቷል።

ወታደራዊ አዛዦቹ የሠራዊቱን ልዩ ልዩ ክፍሎች አኗኗርና አጠቃላይ የግዳጅ ቀጣናውን የጎበኙ ሲሆን፤ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮችና የሠራዊት አባላት ጋርም ውይይት አድርገዋል።

የቡድኑ መሪ ሌተና ጀኔራል አብረሃ ወልደማሪያም በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ዕዙ የተቀበለውን ግዳጅ በሚገባ እየተወጣ መሆኑንን ጠቅሰው ለቀጣይ ከዚህ በበለጠ እንዲሰራ ድጋፍ እንደሚደረግለት አረጋግጠዋል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል መሃመድ ኢሻ ዘይኑ በበኩላቸው የዕዙን የስራ አፈጻጸም ለቡድኑ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ በስራ አፈጻጸም የነበሩ ጥንካሬዎችንና ክፍተቶችንም አብራርተዋል።

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!