መሃንዲስ ዋና መምሪያ ለቡሬ አካባቢ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ አስመረቀ

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ በቡሬ ግንባር አካባቢ ለሚገኙ ነዋሪዎች የገነባውን የመጠጥ ውሃ አስመረቀ።

ዋና መምሪያው የአካባቢው ነዋሪዎች ያለባቸውን የውሃ እጥረት ለማቃለል እና በውሃ ፍለጋ ምክንያት የሚደርስባቸውን እንግልት ለማስቀረት ያለመ ፕሮጀክት በመቅረጽ ነዋሪዎቹ በሚገኙበት በ5 ልዩ ልዩ አካባቢዎች 5 ሺህ ሊትር ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው ላስቲኮችን በማስቀመጥ ቦኖዎችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች አስረክቧል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ሀጂ ስዩም አወል፤  የፕሮጀክቱ ስኬታማነት ሠራዊቱ ትክክለኛ የህዝብ ልጅነቱን ያረጋገጠበት ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

አካባቢው ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንደነበረበት ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ “የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሰራው ስራ የአካባቢው ነዋሪዎችና እንስሳቶቻቸው ያለ ችግር እንዲኖሩ የሚያስችል ነው” ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አያይዘውም፤ እንደዚህ አይነቱ መልካም ተግባር የሠራዊቱንና የህዝቡን ዝምድና የበለጠ የሚያጎለብት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም የውሃ ቦኖዎችንና መስመሮችን ከአደጋ በመከላከል በዘላቂነት ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ መሃመድ ከማል እና አቶ መሃመድ አህመድ በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት፤ በአካባቢያቸው ንጹህ የመጠጥ ውሃ በቅርበት ባለመኖሩ ሲቸገሩ እንደነበር በማስታወስ፤ የሠራዊቱ አባላት በፈጠሩላቸው ዕድል ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

 

 

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ደረጃ ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለሰው ኃብት ልማት ሙያተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ከመከላከያ ሰው ሀብት ዋና መምሪያ...
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ በጦር ሃይሎች ከምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ፡፡
ታህሳስ 26 04 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
ጥር 03 05 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በጀኔራሎቹ ሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በጀኔራሎቹ ሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
ኢትዮጵያውያን ሁሉ በተፈጥሮ ወታደሮች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ደግሞ የተፈጥሮ ወታደርነትን ከዘመናዊ ስልጠናና ከዲስፕሊን ጋር ያዋሀዱ ምርጦች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ይህ ነው...