ከኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ የተሰጠ መግለጫ

 

ከሰሞኑ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በተለያዩ ወረዳዎችና የጠረፍ ደንበሮች በአማራ ብሄረሰብ፤ በኦሮሞ ብሔረሰብ፣ በአገው፣  በሽናሻና በጉምዝ ንፁሃን ዜጎች ላይ የህዝቦችን አብሮነት የማይፈልጉ፣ በግዚያዊ ኩርፊያ የተሰበሰቡና ከተለያዩ የመንግስት የፀጥታ ሀይል በድስፒሊን ግድፈት ምክንያት ከስራቸው የተባረሩና በህገወጥ መንገድ የተሰበሰቡ ሽፍቶች በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሃመድ ተሰማ ተናግረዋል።

መከላከያ የራሱ የሆነ ግዳጅ እና ስምሪት ያለው ሀይል መሆኑን የገለፁት ሜጄር ጄኔራሉ፤ ከሰሞኑ የተከሰተውን ግጭትም የክልሉ መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት ሰራዊቱ በቦታው ፈጥኖ በመድርስ እና በአጥፊዎቹ ላይ እርምጃ በመወሰድ በአካባቢው የተሻለ ሰላም እንዲሰፍን ማድረጉን ሜጄር ጄኔራሉ አብራርተዋል።

ሰራዊቱ በአካባቢው ሰላም እንዲያሰፍን ግዳጅ ከተሰጠው በሁዋላ እልህ አስጨራሽ የሆኑ ጉዙወዎችን በመጓዝና በአጥፊዎቹ ላይ እርምጃ በመወሰድ ከሀያ አምስት ሺ በላይ ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ከማድረጉም በላይ በወንጀለኞች የታገቱ ሀያ ሰባት ዜጉችን ማስመለስ መቻሉን ሜጄር ጄኔራል መሃመድ ተሰማ ገልፀዋል።

የአካባቢው ህዝብም አጥፊዎችን ለሰራዊቱ እያጋለጠ በመስጠቱ በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም መምጣቱን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

በአጠቃላይ ሰራዊቱ ግዳጅ ከተሰጠው በሁዋላ በአካባቢው የህግ የበላይነትን እያሰፈነ እንደሚገኝ ገልፀው፤ በአሁኑ ሰአት በአንዳንድ ሚዲያዎች ስለሰራዊቱ የሚናፈሱ ወሬዎች ትክክለኛነት የጎደላቸው መሆናቸውን አመልክተዋል።

መከላከያ ቋሚ ተልኮዎች ያሉትና በአንዳንድ ክልሎች ለሚፈጠሩ ችግሮች ከክልሉ የፀጥታ ሀይል አቅም በላይ ሲሆን ክልሉ በሚጠይቀው መሰረት መከላከያ ገብቶ የማረጋጋት እና በአጥፊዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ የሚወስድ እና እየወሰደ ያለ መሆኑን ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ አብራርተዋል።

ህብረተሰቡም ከሰራዊቱ ጉን በመሰለፍ አጥፊዎችን አሳልፎ ለመስጠት እያደረገው ያለው አኩሪ ስራ በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም ማምጣቱን ዋና ዳይሬክተሩ ተናገረዋል።

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!