የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር አቢይ አህመድ ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ምንም ያልተነካ አንድ ዓመት ሙሉ ከፊታችን አለን ፤ ብልህ ይመጥቅበታል ሞኝ ይወድቅበታል እኛ ግን ከብልሆዎች ወገን ልንሆን ይገባል፤

- ባገኘናቸው ድሎች ረክተን አንቀርም ባሳለፍናቸው ድሎች ታስረን አንቆምም ወደ ልዕልና እንመጥቃለን፤

- 2012 በደስታና ሀዘን ፣ በክብርና ውርደት፣ በኩራትና ሀፍረት የተሞላ ዓመት ነበር ፤

-የኢትዮጵያ ፈታኞች ፣ አሉን ያሉትን ድንጋዮች ሁሉ ወርውረዋል ፤ ሆኖም የኢትዮጵያ ጀግኖች የቻሉትን ሁሉ ለሀገራቸው ሰውተዋል ፤ ትርፍ ነብስ ያላቸው እስከሚመስል በጀግኖቿ ብርታት መከራውን ሁሉ አልፋ ኢትዮጵያችን ዛሬም አለች ፤

- ኢትዮጵያ ጨለማ የማይበግራት የብርሃን ሀገር ፣ የብርቱ ህዝብ የፅኑ ዜጋ ሀገር ናት ፤

- ከጨለማ በኋላ ብርሃን ፣ ከፈተና በኋላ ተስፋ ፣ ከመለያየት በኋላ መገናኘት ፣ ከውድቀት በኋላ መነሳት አለ ፤

- ከዘመን ወደ ዘመን የምናደርገው ሽግግር ትርጉም እንዲኖረው ካለፈው ዘመን ጋር አሮጌና ጎታች አስተሳሰባችንን ተሰናብተን አዲስ እና ተራማጅ አስተሳሰብን ልንላበስ ይገባል ፤

- መጪው ዓመት ስላለፈው የምንቆዝምበት ፣ ስላለፈው ቂም ቋጥረን በቀልን የምናስብበት ሳይሆን በይቅርታ እና በእርቅ ሰላምን አውርደን በመተሳሰብና በመደማመጥ ልዩነታችንን አጥብበን ህዝባችንን እና ሀገራችንን በማስቀደም ወደ ልዕልና የምንመጥቅበት እንዲሆን ሁላችሁንም እጋብዛለሁ ።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!