የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ

በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፤ የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጀኔራል መሃመድ ተሰማ እንዲሁም የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጎሳየ ሽፈራው ተገኝተዋል ፡፡

በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ እንደገለፁት ፤ ሰራዊቱ በህብረተሰቡ ውስጥ በሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ ህዝቡን የማገዝ ተግባሩ የነበረ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

ሰራዊቱ የመደጋገፍ ባህሉ በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን በተሰማራበት የሰላም ማስከበር ግዳጂ ላይም በአካባቢው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ህዝባዊነቱን እያስመሰከረ ይገኛል ብለዋል።

የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጀኔራል መሃመድ ተሰማ በበኩላቸው ፤ ሴት የሰራዊት አባላት ያደረጉት ድጋፍ የአብሮነታችን እና የፍቅር ስጦታ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል እንደሁነ አብራርተዋል።

ሰራዊት ያለ ህዝብ ትርጉም የለሽ በመሆኑ እንዲህ አይነት የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህሉም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጎሳየ ሽፈራው በበኩላቸው ፤ ሰራዊቱ ከህዝብ አብራክ ወጥቶ ለህዝቦች ሰላም ፣ አንድነት እና ፍቅር መተኪያ የሌለውን ውድ ህይወቱን አሳልፎ እየሰጠ በተግባር ሀገር እና ህዝቡን በቁርጠኘነት እያሻገረ ያለ እና በሁሉም የግዳጅ ቀጣና ተወዳጅነትን እያተረፈ ያለ ነው ብለዋል ።

ሰራዊቱ የክፍለ ከተማውን አቅመ ደካሞች ሲያግዝ ይህ የመጀመርያው ሳይሆን ከዚህ በፊትም የፈራረሱ ቤቶችን በመጠገን እና መሰል ተግባሮችን በማከናወን ህዝባዊነቱን አስመስክሯል ብለዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ወቅቱን ያገናዘበ ድጋፍ ስለተደረገላቸው ለሰራዊቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና...
ነሐሴ 26 12 2012 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ነሐሴ 17 12 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ ፣ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል...
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፤ የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር...