በልዩ ልዩ የሠራዊቱ ክፍሎች ሲካሄዱ የቆዩት የስፖርት ፌስቲቫሎች ተጠናቀቁ

በልዩ ልዩ የሠራዊታችን ክፍሎች ሲካሄዱ የቆዩት ስፖርታዊ  ውድድሮች በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቁ።

ስፖርታዊ ውድድር ለተሻለ የተልዕኮ አፈጻጸም በሚል መሪ መፈክር በ1ኛ አግአዚ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አዘጋጅነት ከመስከረም 14 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የስፖርት ፊስቲቫል በአዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲዮም በተለያዩ ፕሮግራሙን በሚያደምቁ ዝግጅቶች ተጠናቋል።

በክብር እንግድነት የተገኙትና ለአሸናፊዎች የዋንጫ ሽልማትና ሰርተፊኬት በመስጠት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ሜጄር ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና በአዋሳ አካባቢ የሚገኘው የሠራዊት ዋና አዛዥ ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ በንግግራቸው የክፍሉ ስፖርታዊ ውድድር ለአሃዱ መቀራረብና ዝግጁነት ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን አውስተው፤ በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑንና በትኩረት ሊሰራበት ከተቻለ የተቋሙን ቁልፍ እሴት በመላበስ በዲሲፕሊን የታነፀ እና ጠንካራ አካላዊ ብቃት ያለው ግዳጅን በተቀመጠለት አቅጣጫና ግብ መሰረት መፈጸም የሚችል ሠራዊት ለመገንባት ስፖርታዊ ውድድር ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤል የ1ኛ አግአዚ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ በበኩላቸው፤ ስፖርታዊ ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ የታለመለትን ግብ እንዲመታ ሬጅመንቶች ያሳዩትን መነሳሳት መንግስትና ህዝብ የሚሰጡንን ተልዕኮ በላቀ ውጤት መፈጸም የሚያስችል ዝግጁነት ለመገንባት ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።

አጠቃላይ የስፖርታዊ ውድድሩን ዓላማና ግብ በተመለከተ በዕለቱ ሪፖርት ያቀረቡት ደግሞ የክፍለ ጦሩ ኢንዶክትሪኔሽን ቡድን መሪ ሌተና ኮሎኔል አለምሰገድ ወልደገሪማ ሲሆኑ፤ ስፖርት ለሠላምና ለልማት ካለው ጠቀሜታ ባሻገር በተለይ ለሠራዊት አሃዳዊ ዝምድና ለማሳደግና የክፍልን ፍቅር ለመገንባት አይነተኛ መሣሪያ መሆኑን ገልጸው፤በዕቅድ እና በነጠረ አቅጣጫ መከናወን እንደሚገባው አበክረው አስገንዝበዋል።

በስፖርት ፌስቲቫሉ ማጠቃለያ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ሲቪል የማህበረሰብ ክፍሎችና አመራሮች እንዲሁም በአካባቢው የሚኖሩ የሠራዊት አባላት በእንግድነት የታደሙ ሲሆን፤ የካታ ትርዕይት፣ አዝናኝ እና አስተማሪ የሠራዊትን ሥነ-ልቦና በመገንባት ለሰላምና ለዝግጁነት ወኔን የሚቀሰቅሱ ዝግጅቶች ቀረበዋል። ውድድሩም በአሸናፊዎች አሸናፊ አጠቃላይ ውጤት በሰርዶ ሬጅመንት የበላይነት ተፈጽሟል ሲል የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ም/መቶ አለቃ ክብሮም ጌታቸው ዘግባ ያስረዳል።

በተያያዘ ዜና በ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 5ኛ ሓየሎም ሬጅመንት በሻምበሎች መካከል በአራት ምድብ በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በሩጫ፣ እና በገመድ ጉተታ ለሁለት ወር ያህል ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።

በውቅሮ ከተማ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ በተካሄደው የውድድሩ ማጠቃለያ ሥነ- ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ለፍፃሜ የደረሱ ሻምበሎችን ውድድር በማስጀመር በውጤቱ መሰረት ለአሸናፊዎች የተዘጋጀውን ሽልማት በመስጠት የመመሪያ ንግግር ያደረጉት የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሃድሽ ገብረስላሴ ናቸው።

ዋና አዛዡ  በንግግራቸው እንደገለጹት፤ ስፖርት በተለይ ለመከላከያ ሠራዊቱ ከተልዕኮው ጋር የተያያዘ በመሆኑ አካላዊ ጥንካሬን ለመገንባትና በአሃዱዎች መካከል አንድነትና ፍቅርን ለመፍጠር እንደሚረዳ ጠቁመው፤ ስፖርት በጤናው ዘርፍም በሽታዎችን ለመከላከል የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።

የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት ልማት ሻለቃ አለሙ ኪንኪና በበኩላቸው፤ ስፖርታዊ ውድድሩ በዋናነት ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለማፍራትና የሻምበሎችን የእርስ በርስ ዝምድና ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በክፍለ ጦር ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር የተሻለ ውጤት ለማምጣት የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ተሸላሚ ከሆኑት የሠራዊት አባላት መካከል ሻምበል ባሻ ሙሉቀን ዲብሳ፣ ፲ አለቃ በሪሁን ኃይሌ እና ም/፲ አለቃ ወርቁ ጌትነት በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት ባስመዘገቡት የተሻለ ውጤት ለሽልማት በመብቃታቸው እንደተደሰቱ ገልጸው፤ ቀጣይም በስፖርቱ ዘርፍ ሀገር የመወከል ራዕያቸውን ለማሳካት ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ስፖርታዊ ውድድሩም በሻምበል 4 አጠቃላይ ዋንጫ አሸናፊነት ተጠናቋል ሲል የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፶ አለቃ ካሳሁን አጥናፉ  ከስፍራው ዘግቧል።

በሌላም ዜና በአካል ብቃቱ የዳበረ ስፖርተኛን ከማፍራት ባሻገር የሠራዊቱን አንድትና የእርስ በርስ ግንኙነቱን ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ  መሆኑን የ33ኛ አባይ ክፍለ ጦር ኢንዶክትሪኔሽን ቡድን ኃላፊ ሌተና ኮሎኔል ሽፈራው ቢሊሶ ተናገሩ።

ይህንን የተናገሩት በ336ኛ ሬጅመንት ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲካሄድ በቆየው የስፖርት ፌስቲቫል የመዝግያ ፕሮግራም ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑት ሽልማት በሰጡበት ወቅት ነው።

በእግር ኳስ፣ በሴቶች 800 ሜትር ሩጫና በወንዶች 300 ሜትር ሩጫ ሲካሄድ በነበረው ስፖርታዊ ውድድር በመልካም ሥነ-ምግባር በመታነጽ ከራሱ በፊት ለህዝብና ለሀገሩ ቅድሚያ ለሚሰጠው ሠራዊታችን ለአንድነታቸው መገለጫ ይሆናል ያሉትን የሬጅመንቱ አባላት በሙሉ አንድ አይነት ማልያ በመግዛትና መጠሪያቸውን ከጀርባ በማሳተም እንዲሁም “እኛ አንድ ነን ለአንድ ዓላማ ለአንድ ሃገርና ለህገ -መንግስት ዘብ የቆምን ነን”  በማለት አንድነታቸውን አንጸባርቀዋል። 

በውድድሩም በእግር ኳስ 5ኛ ሻምበል አንደኛ ስትወጣ፣ 3ኛ እና 2ኛ ሻምበል 2ኛና 3ኛ ሆነው ውድድራቸውን ሲያጠናቅቁ፣ በሴቶች 800 ሜትር ሩጫ  4ኛ ሻምበል 1ኛ ስትወጣ ሬጅመንት ስታፍ 2ኛ እንዲሁም በወንዶች 300 ሜትር ሩጫ 3ኛ ሻምበል 1ኛ፣ 5ኛ ሻምበል 2ኛ፣ 3ኛ ሻምበል 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል ሲል የክፍለ ጦሩ  ሪፖርተር % አለቃ እንግዳ ታደሰ ዘግቧል።

ይህ በእንዲ እንዳለ በማዕከላዊ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር በ4ኛ ሬጅመንት በሻምበሎች መካከል ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።

በስፖርታዊ ውድድሩ ማጠቃለያ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ሻምበሎች የተዘጋጀላቸውን የገንዘብ ሽልማት ከሰጡ በኋላ ንግግር ያደረጉት የ224ኛ ሬጅመንት አዛዥ ተወካይ ሻለቃ ተስፋዬ ይተይ ናቸው።

ከፍተኛ መኮንኑ በንግግራቸው ስፖርታዊ ውድድሩ የእርስ በርስ ግንኙነትና ጓዳዊ ዝምድናን ከማጠናከሩም ባሻገር ወታደራዊ የአካል ብቃትን የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ ስፖርታዊ ውድድሩ በቀጣይነትም ከግዳጃችን ጎን ለጎን ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው የዘውትር ተግባር ነው ብለዋል።

ውድድሩ እግር ኳስና መረብ ኳስን ያካተተ ሲሆን፤ በመረብ ኳስ ለፍፃሜ ጨዋታ አንደኛ ሻምበልና ሁለተኛ ሻምበል ተገናኝተው በሁለተኛ ሻምበል 3 ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል። በእግር ኳስ በተካሄደው የማጠቃለያ ጨዋታ ሁለተኛ ሻምበል ከአምስተኛ ሻምበል ጋር ተጫውተው አምስተኛ ሻምበል 2 ለ1 በሆነ ውጤት በመርታት ውድድሩ መጠናቀቁ ተገልጿል  ሲል የሬጅመንቱ ሪፖርተር ፲ አለቃ ባባው ዘውዴ ዘግቧል።

በተመሳሳይ ዜና በ305ኛ ሬጅመንት እየተካሄደ የነበረው የስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ።

ስፖርታዊ ውድድሩ በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በመረብ ኳስ፣ የተካሄደ ሲሆን፤ በሴቶች በ200 ሜትር የሩጫ ውድድር ወ/ር አዘለች አመሎ፣ ጫልቱ ዳሌ፣ ርብቃ አለቶ ከ አንድ እስከ ሦስተኛ ሲወጡ በ400 ሜትር ደግሞ ወ/ር ካሰች ተሰማ፣ አረጉ መስቀሉ፣ ጫልቱ ዳሌ ከአንድ እስከ ሦስት ወጥተዋል።

በወንዶች በተካሄደው 100 ሜትር ሩጫ ውድድር ወ/ር ናስር አብድቃድር፣ ሽርሌ ኩታ፣ አብድናስር አልየ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ወጥተዋል። በ200 ሜትር የሩጫ ውድድር ፶ አለቃ ናስር አልይ፣ ፲ አለቃ ባየ ፍሬው፣ ፲ አለቃ ዙፋን ጩፋሞ፣ ከአንድ እስከ ሦስት ወጥተዋል።

በመረብ ኳስ ሻምበል አንድ ሬጅመንት ስታፍን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሲሆን ፤ በእግር ኳስ 4ኛ ሻምበል እና 3ኛ ሻምበል ባደረጉት የዋንጫ ጨዋታ በመደበኛው ሰዓት ባለመጠናቀቁ በፍጹም ቅጣት ምት ሻምበል አራት  5 ለ3  በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

ለአሸናፊዎችና በስፖርት ውድድሩ ጥሩ እንቅስቃሴ ለነበራቸው ግለሰቦችና ክፍሎች ዋንጫና ሰርተፊኬት ከሰጡ በኋላ ንግግር ያደረጉት የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ሻለቃ ይልማ አብርሃ መሆናቸውን  የሬጅመንቱ ሪፖርተር ፲ አለቃ መላኩ ረታ ዘግቧል።

በሌላም በኩል በ333ኛ ሬጅመንት ለተከታታይ 3 ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።

በቀጣይ በክፍለ ጦር ደረጃ ለሚደረግ የስፖርት ፌስቲቫል ሬጅመንቱን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለመመልመል በተካሄደው በዚህ ስፖርታዊ ውድድር በእግር ኳስ፣ በሴቶች አራት መቶ ሜትር እንዲሁም በወንዶች የስምንት መቶ ሜትር አትሌቲክስ ውድድር ተካሂዷል።

በወንዶች እግር ኳስ በተደረገ ውድድር የሬጅመንት ስታፍ እና ሻምበል አንድ ለፍጻሜ የደረሱ ሲሆን፤ ሬጅመንት ስታፍ ሻምበል አንድን አራት ለሦስት ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ለመሆን በቅቷል።

ዋንጫውን ለአሸናፊዎች ያስረከቡት የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተና ኮሎኔል ዘነበ ሃመልማል ናቸው። አዛዡ ስፖርታዊ ውድድሩን በፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነትና ወታደራዊ ዲስፕሊን መጠናቀቁን ም/፲ አለቃ ብሩ መለሰ ያደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!