በሰሜን ዕዝ የ20ኛ ቃሉ ክፍለ ጦር ሥራ አመራር ቡድን የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ሙያተኞችን አስመረቀ።

በሰሜን ዕዝ የ20ኛ ቃሉ ክፍለ ጦር ሥራ አመራር ቡድን ለአሥር ተከታታይ ቀናት ሲያሰለጥናቸው የቆየውን የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ሙያተኞችን አስመረቀ።

በዕለቱ የ20ኛ ቃሉ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ኑሩ ሙዘይን እንዲሁም የሰሜን ዕዝ የሥራ አመራር ዳያሬክቶሬት ዳይሬክተር በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ዋና አዛዡ ብርጋዴር ጀነራል ኑሩ ሙዘይን በሥልጠናው ብልጫ ላመጡ ሙያተኞችና አሃዱዎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ካበረከቱ በኋላ በሳሙት የሥራ መመሪያ ንግግር ፣ የሠራዊቱን ግዳጅ ስኬታማ በማድረግ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማቀላጠፍ የሙያተኛው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

አያይዘውም በስልጠናው የቀሰማችሁትን እውቀት ተግባር ላይ በማዋል ለተሻለ ውጤት መሰራት ይጠበቅባችአል ሲሉ አሳስበዋል።

የክፍለ-ጦሩ ሥራ አመራር ቡድን ሌ/ኮ አብረሃለይ ወልደ ገብርኤል ባቀረቡት የፅሁፍ ሪፖርት ፣ ከዚህም ቀደም የነበረውን የስራ ክፍተት ለመሙላትና የሙያተኛውን አቅም ለማሳደግ በተለያዩ ርዕሶች ትኩረት የተደረጉ የፋይናንስ ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር ስልጠናዎች ሰጥተን በአዲሱ በጀት ዓመት የተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ዝግጁ ነን ብለዋል።

መቶ አለቃ እያሱ ብርሃኑ ፣ ም/፲/አ ዘውዴ ሰንደቁ እና ወታደር ፍቃዱ አስማረ በሰጡት አስተያየት ፣ በስልጠናው በቂ እውቀት ማግኘታቸውን አስታውሰው ይህንኑ ክህሎታችውን በስራ ለማሳየትና ለበለጠ ውጤት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና...
ነሐሴ 26 12 2012 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ነሐሴ 17 12 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ ፣ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል...
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፤ የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር...