የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ ፣ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል ጠንካራ ሀይል መገንባት መሆኑን አስታወቁ ።

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል ።

በስነ ስርዓቱ ላይ ጀነራል አደም መሀመድ እንደተናገሩት ፣ የሀገራችንን ሉዓላዊንትና የህዝባችንን ደህንነት ለመጠበቅ ወታደራዊ አመራሮች በዕውቀት ላይ ተመስርተው ሀገርን እና ህዝብን ማገልገል ይጠበቅባቸዋል ።

የኮሌጁ ኮማንዳንት ብ/ጀ ዳኛቸው ይትባረክ በበኩላቸው ፣ በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ስልታዊ አመራር ዘጠና ስልጣኞች ሲመረቁ ፣ አስራ ስምንቱ ከ አምስት የጎረቤት ሀገር የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጀ ሀሰን ኢብራሂምን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!