የኮቢዲ-19/ኮሮና ቫይረስ/ ወቅታዊ መረጃ

የ‘አንቲ-ቦዲ’ ምርመራ ምንድነው?

የአንቲ-ቦዲ ምርመራ ኮቪድ-19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ዳሰሳ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ቢኖረውም ከምርመራው የሚገኘውን ውጤት ብቻ ተጠቅሞ ህክምና መስጠት አይቻልም፡፡

ለመሆኑ የአንቲ-ቦዲ ምርመራ ምንድነው? ለምንስ ያገለግላል ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያገኛቸውን መረጃዎች በሚከተለው መልኩ አጠናቅሯቸዋል፡፡

አንቲ-ቦዲ ወይም ጸረ-እንግዳ አካል ምንድነው?

አንቲ-ቦዲ ወይም ጸረ-እንግዳ አካል በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ የፕሮቲን ቅንጣቶች ናቸው፡፡ ሰውነታችን ራሱን ከበሽታዎች እንዲጠብቅ እና ቀደም ሲል ይዞን በነበረው በሽታ ዳግም እንዳንጠቃ የሚከላከሉልን ወይም የሚያድኑን ናቸው፡፡

ሰውነታችን ሊያዘጋጅ የሚችለው መድህን (immunity) ግን እንደየ በሽታዎቹ ዓይነት ይለያያል፡፡ ሰውነታችንን ክፉኛ ከተጠቃን በኋላ ሊያዘጋጅ የሚችለው ጸረ-እንግዳ አካል ከሌላ በሽታ ሊያድነን ግን አይችልም፡፡

እንዴት ይካሄዳል?

የአንቲ-ቦዲ ምርመራም በዋናነት የደም ናሙናዎችን በመውሰድ የሚካሄድ ነው፡፡ ከ3-5 ሚሊ ሊትር ደም ናሙናዎችን በመውሰድ ይካሄዳል፡፡ በደም ውስጥ ያሉት አንቲ-ቦዲዎች ናቸው ከአሁን ቀደም ኮቪድ-19 በሚያስከትለው ቫይረስ ተይዘን እንደሆነ ለማወቅ በሚያስችል መልኩ የሚመረመሩት፡፡

ምርመራው ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ዳሰሳ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ሆኖም ከምርመራው የሚገኘውን ውጤት ብቻ ተጠቅሞ ህክምና ለመስጠት አይቻልም፡፡ ቀጥታ በቫይረሱ መያዛችንንም ሳይሆን ከአሁን ቀደም ተይዘን እና ሰውነታችን መድህኖችን (immunities) አዘጋጅቶ እንደሆነ ለማወቅ ብቻ የሚደረግ የምርመራ ዓይነት ነው፡፡

አንድ ሰው በቫይረሱ መያዝ አለመያዙን ለማረጋገጥ የቫይረስ ምርመራ (Viral Test) ነው የሚደረገው፡፡ ምርመራው አፍና አፍንንጫችንን ከመሳሰሉ የስርዓተ ትንፈሳ አካላት ናሙናዎችን በመውሰድም ይካሄዳል፡፡ የምርመራው ውጤትም ከአንድ እስከ ሁለት ቀናት ውስጥ ይታወቃል፡፡ የአንቲ-ቦዲ ምርመራ ግን ዘለግ ያለ ጊዜን ሊወስድ ይችላል፡፡

የአንቲ-ቦዲ የምርመራ ውጤቶች ምንን ያሳያሉ?

አንቲ-ቦዲን በመመርመር የሚገኙ ውጤቶች ቀደም ሲል እንደተገለጸው ሁሉ ከአሁን ቀደም ኮቪድ-19 በሚያስከትለው ቫይረስ ተይዘን እንደሆነ ለማወቅ የሚያስችሉ ናቸው፡፡ ውጤቱ ፖዘቲቭ የሚሆን ከሆነ ከአሁን ቀደም ኮቪድ-19ን በሚያስከትለው ቫይረስ አለበለዚያም ጉንፋን ኢንፍሉዌንዛን በመሳሰሉ ተመሳሳይ የቫይረስ ዝርያዎች ተይዘን እንደነበር የሚያመላክት መሆኑን ከአሜሪካ የበሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል የተገኙት መረጃዎች ያረጋግጣሉ፡፡

ሆኖም ከአሁን ቀደም ኮቪድ-19ን በሚያስከትለው ቫይረስ ተይዘን ሰውነታችን ያዳበራቸው አንቲ-ቦዲዎች አሁንም ቫይረሱን ለመከላከል ያስችሉን አያስችሉን እንደሁ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ እስከመቼ ለመከላከል ያስችላሉ ስለሚለውም ገና አልታወቀም፡፡

የምርመራ ውጤታችን ኔጌቲቭ የሚሆን ከሆነ ከአሁን ቀደም ኮቪድ-19 በሚያስከትለው ቫይረስ አልተያዝንም ነበር ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ይህ አሁንም ላለመያዛችን ዋስትና አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ሰውነታችን አንቲ-ቦዲውን ለማዘጋጀት እስከ ሶስት ሳምንታት ሊወስድበት ይችላል፡፡

ምናልባትም አንቲ-ቦዲው በሚዘጋጅባቸው በነዚሁ ሳምንታት የምንጋለጥበት አጋጣሚ ካለ በቫይረሱ ልንያዝ ወደ ሌሎች ልናስተላልፍም እንችላለን ማለት ነው፡፡ በዋነኛት ከቅርብ ጊዜ ወድህ አዲሱን ቫይረስ የመከላካል ጥረታችን (ትጋታችን) መዘናጋት እየታየበት ይገኛል፡፡ በሽታው አደገኛ በኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ ታላላቅ ሃገራትንም ጭምር ሳይቀር አገንገት እያስደፋ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢሆን የበሽታውን የመከላከል ተግባራችንን ሳንሰላች አጠናክረን በመቀጠል እኛ ቆመን ለህዝባችንና ለሀገራችን አለኝታ መሆን ይኖርብናል፡፡

 

ምንጭ፡- https://am.al-ain.com/article/ethiopia-starts-conducting-nationwide-covid-19-antibody-testing

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና...
ነሐሴ 26 12 2012 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ነሐሴ 17 12 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ ፣ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል...
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፤ የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር...