10ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን በደማቅ ስነ-ስርዓት ተከበረ

“ሠንደቅ ዓላማችንን በማስቀደም በድህነትና ኋላቀርነት ላይ ባደረግነው ዘመቻ በርካታ ሀገራዊ ድሎች ተመዝግበዋል” በማለት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አረጋገጡ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያረጋገጡት 10ኛው የኢፌዴሪ ሠንደቅ ዓላማ ቀን በብሄራዊ ደረጃ በአዲስ አበባ ስታዲየም  በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በተከበረበት ወቅት በክብር እንግድነት ተገኝተው ለበዓሉ ታዳሚዎችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

“የነፃነታችን ምልክት የሆነው ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያውያን የተለየ ትርጉም አለው ያሉት ፕሬዝዳንቱ የሁሉንም ህዝቦች ፍላጎት መሠረት አድርጎ የፀደቀው ህገ-መንግሥታችን ላይ የተደነገገው ሠንደቅ ዓላማችን የዴሞክራሲያዊ አንድነታችን መገለጫ፣ የልማት ትግሉና ውጤቱ ዓርማ መሆኑን አመልክተዋል።

ነፃነቱን ጠብቆ ለኖረ ህዝብ ረሃብ፣ ድህነትና ስደት ከሞት በላይ የከበዱ መሆናቸውን የገለጹት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ይሄን አስከፊ ስም ለመቀየርና ወደነበርንበት የክብር ማማ ለመመለስ ትውልዱ ለሠላም፣ ልማትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትግል ጀምሯል፣ በድህነትና ኢ-ፍትሃዊነት ላይ ዘምቷል፣ በመሆኑም በአብነት የሚጠቀስ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ በዲፕሎማሲያዊ መስክ ከፍተኛ ተደማጭነትና ሌሎች ድሎችን  ማስመዝገብ መቻሉን አስረድተዋል።

የተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ክብርት ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው፤ ለፓን-አፍሪካዊነት አስተሳሰብ መገለጫ የሆነው ሠንደቅ ዓላማችን በነበረው ግዙፍ ታሪክ ላይ ዴሞክራሲያዊ እሴት ጨምሮ በምንነትና ትርጓሜ እንዲሁም በአጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለማሳደግ የሠንደቅ ዓላማን ቀን ከማክበር ባለፈ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን አሳውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ አባተ ስጦታው የብዝሃነታችን ዓርማ፣ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችን መገለጫ በሆነው የሠንደቅ ዓላማችን ቀን ላይ ለተገኙና ለበዓሉ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት አካላት ምስጋናቸውን ካቀረቡ በኋላ የሠላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶቻችን ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት አሳስበዋል።

በበዓሉ ላይ ከ30 ሺህ የሚልቁ የከተማው ነዋሪዎች ፣ የኢፌዴሪ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አርበኞች፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላትና ተቋማት ሠራተኞች ተገኝተዋል።

ለበዓሉ ድምቀት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን ለሠንደቅ ዓላማ ዘላቂ ክብር ዜጋው በተሰማራበት የሥራ መስክ ሁሉ ውጤታማ መሆን እንደሚገባው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተያየት ሰጥተዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስተራክሽን ኢንተርፕራይዝ  በ2011 የበጀት አመት በርካታ ዉጤታማ ስራዎች ማከናወኑ ተገልጿል፡፡
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና