መከላከያ ለሰው ሀብት ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቷል

መከላከያ ለሰው ሀብት ልማት ሥራ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱንና ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን የትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተና ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ገለጹ።

ኃላፊው ይህንን የገለጹት የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና የበታች ሹም ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች ሰሞኑን ባስመረቀበት ወቅት በክብር እንግድነት በመገኘት በሂደቱ ብልጫ ላመጡ አሠልጣኞችና ሠልጣኞች ሽልማት ከሰጡ በኋላ ባደረጉት የመመሪያ ንግግር ነው።

የመከላከያ ሰራዊቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ህዝባዊ ባህርይ ተላብሶ እያሳካ በሠላም ማስከበር በተሰማራባቸው ጎረቤት ሀገራት ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱንና አሁንም ማንኛውንም ተልዕኮ ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑን ያወሱት ጄኔራል ሰዓረ፤ “በሙሉ ፈቃድ ተቋሙን በመቀላቀል፣ ሙያው የሚጠይቀውን ብቃት በመላበስ ለምርቃ የበቃችሁ አባላት በምትሰማሩበት ክፍል ሙያው የሚጠይቀውን ፅናት፣ ዲስፕሊን፣ ቆራጥነት፣ ታታሪነት፣ ታማኝነትና በራስ መተማመን መንፈስ ተላብሳችሁ ተልዕኳችሁን መወጣት ይጠበቅባችኋል” ብለዋል።

የማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ፍስሐ በየነ በበኩላቸው፤ ማሠልጠኛው ከሁሉም የሀገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የመከላከያን መስፈርት አሟልተው የተመለመሉ ወጣቶችን ተቀብሎ በመሠረታዊ ውትድርና ሙያ የማብቃት ኃላፊነቱን በሚገባ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎች በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ የግንባታና ወታደራዊ ሥልጠና ተከታትለው የተቀመጡ የመመረቂያ መስፈርቶችን አሟልተው ለምርቃ መብቃታቸውን የተናገሩት ጄኔራል መኮንን የተቋሙ የለውጥ እንቅስቃሴ ዋና ማዕከል የሰው ኃይል ልማት በመሆኑ ሥራው በላቀ ብቃት እንዲቀጥል ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ አቅም በማሳደግ፣ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ በማከናወ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽ን፣ በየሥልጠና ምዕራፍ ግብረመልስ በመቀበል የማሠልጠን ብቃቱን ከፍ ማድረጉን ጠቁመዋል።

የሥልጠናው ወቅት ክረምትና ከፍተኛ ዝናብ የነበረበት በመሆኑም ሥልጠናውን ከባድ አድርጎት እንደነበር ያስታወሱት የማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ አዛዥ ነገር ግ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽ን ሠልጣኞቹ ሁሉንም መሰናክል አልፈው  በዕውቀት፣ በችሎታ፣ በአስተሳሰብና ባህሪይ ታንፀው ለምረቃ ማብቃታቸውን አረጋግጠዋል። 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ
የመከላከያ ኮንስተራክሽን ኢንተርፕራይዝ  በ2011 የበጀት አመት በርካታ ዉጤታማ ስራዎች ማከናወኑ ተገልጿል፡፡
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና