የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ አቅሞች

የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ አቅሞች

 ዜና ትንታኔ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ህዝብና መንግሥት የሰጡትን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ ይገኛል። ይህን ለማጠናከር ለዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ መሠረት የሚጥሉ በርካታ ሥራዎች እየሰራ ነው። በተለይም በሠራዊቱ ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊነትና ጠቀሜታ ያላቸውን የመሰረታዊ ባሻ ሥልጠና በመስጠት የበታች ሹሙ ብቁ አመራር እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል።

መከላከያ ባሉት የሥልጠና ተቋማት የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ብቃት የሚያሳድጉ ሥልጠናዎች በመሰጠቱ አባሉ ግዳጁን በላቀ ብቃት እንዲወጣ አስችሎታል።

የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ብቃት ከሚያሳድጉ የሥልጠና ተቋማት አንዱ የጦላይ የከፍተኛ የበታች ሹም ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት አንዱ ነው። ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ ለህገ-መንግሥቱ፣ ለሠራዊቱ ደንቦችና መመሪያዎች ተገዢ የሆነ የበታች ሹም በሥልጠና እያበቃ ነ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽ው።

ሀገራችን በድህነት ላይ የምታደርገው ጥረትና ፈጣን የልማት ዕድገት ግለቱን ጠብቆ እንዲጓዝ የተረጋጋ ሠላም በእጅጉ ያስፈልጋል። አስተማማኝ ሠላምን ለማረጋገጥ በማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሚሰለጥኑት የበታች ሹሞችም በሠላምም ሆነ በውጊያ ጊዜ ሠራዊት በማሰልጠን፣ በማስተዳደር፣ በመገንባት፣ በመምራት፣ በስልታዊ ተመጣጣኝ ክፍሎች ሎጀስቲካዊ ድጋፍ መስጠት ይችላሉ።

ከፍተኛ የበታች ሹም ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ በ21 ዙር ከፍተኛ የበታች ሹሞችን አስመርቋል። በሠራዊቱ ውስጥ እንደ ጀርባ አጥንት የሚያገለግሉና በሠራዊት የግንባታ ሥራና የውጊያ ዝግጁነት ውስጥ የማይተካ ሚና የሚኖራቸው በርካታ ብቁና ጠንካራ የበታች ሹሞች አፍርቷል።

የጦላይ የከፍተኛ የበታች ሹሞች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለ21ኛ ጊዜ ሰሞኑን ሠልጣኞችን ሲያስመርቅ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ በሥልጣና ሂደት ውጤታማ  ለሆኑ አሰልጣኞችና ሠልጣኞች  የተለያዩ ሽልማቶችን ሰጥተዋል። ማዕረግም አልብሰዋል። ሥልጣናቸውን ላጠናቀቁ ተመራቂዎች የመመሪያ ንግግር አድርገዋል።

ኃላፊው ባደረጉት ንግግርም፣ ህገ- መንግሥቱንና ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከፀረ-ሠላምና ከፀረ -ልማት ኃይሎች በመጠበቅ በሀገሪቱ ፈጣን ልማትና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለእንቅፋት እንዲቀጥል ማድረግ የሚቻለው ቀጣይነት ያለው አስተማማኝ ሠላም ማረጋጋጥ ሲቻል ነው ብለዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትም ህገ-መንግሥታዊ ተልዕኮውን በአስተማማኝ እየተወጣ ይገኛል። ለተልዕኮው ስኬትም ሁሉን አቀፍ ዝግጅት ያደርጋል ያሉት ሌ/ጄኔራል ሰዓረ፤ ከዝግጅቶችም በዕውቀት፣ በክህሎት፣ በአስተሳሰብና በባህሪይ የታነፀ፣ የሚሰጠውን ግዳጅ በሚገባ መወጣት የሚችል ከመሠረታዊ ወታደር እስከ ከፍተኛው አመራር ድረስ ማስተማርና ማሰልጠን  እንደሆነ አስረድተዋል።

ከፍተኛ የበታች ሹሞች የታችኛውን የበታች ሹም ከመኮንኑ ጋር እንደ ድልድይ የሚያገናኙ፣ በደረጃቸው የሚገነቡ፣ የሚያሰለጥኑ፣ የሚደግፉና ለድል የሚያበቁ በመሆናቸው በተከታታይ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የከፍተኛ የበታች ሹም ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ኮሎኔል መንግሥቱ ተክሉ በዕለቱ ባቀረቡት የሥልጠና ሪፖርት ሠልጣኙ በተቀመጠው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ወታደራዊ ብቃት እንዲላበስ የሚያደርጉ ሥልጠናዎችን ተከታት﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽ል። በየሥልጠና ሂደቱም እየተመዘገበ አጥጋቢ ውጤት መምጣቱ ተረጋግጧል።

ተቋሙ የተሰጠውን ህገ-መንግሥታዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት አስተማማኝ ሠላምን ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት ተመራቂ ከፍተኛ የበታች ሹሞች በየክፍላቸው ሲሄዱ የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ ዋና አዛዥ ሙሉ እምነታቸው መሆኑን  ገልፀዋል።

የጦላይ ከፍተኛ የበታች ሹም ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ከመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያና ባለድርሻ አካላት ጋር ሥርዓተ ትምህርቱን የማሻሻል ሥራ እየተሰራ ይገኛል። በቀጣይም ሙያዊ ክህሎት የተላበሱ፣ በተለይም በውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ዘርፍ በደረጃቸው የሚመሩ ከፍተኛ የበታች ሹሞችን እንደሚያፈራ ይጠበቃል።

 

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!