የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጀኔራል መኮንኖችን ሾሙ፡፡

 

የማዕረግ ሹመቱ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አቅራቢነት የተከናወነ ሲሆን፤ 6 ሌ/ጀኔራሎች፣ 19 ሜ/ጄኔራሎችና 40 ብ/ጄኔራሎች ተሹመዋል፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ በክብር እንግድነት ተገኝተው ለጄኔራሎቹ ማዕረግ በማልበስ የመመሪያ ንግግር ባደረጉበት ጊዜ፤ ጀኔራሎቹ አብዛኛውን ዕድሜያቸውን ብሎም መተኪያ የሌላት ሕይወታቸውን ለሀገር ክብርና ሉዓላዊነት በመስጠትና ለዚህም ክብር መብቃት ያለውን እርካታና ከባድ ኃላፊነት ‘’በውትድርና ቤት ያደኩኝ በመሆኑ ጭምር በእጅጉ እገነዘባለሁ” ብለዋል፡፡

ከፍተኛ የማዕረግ ሹመቱ ሁለት ዓበይት መልዕክቶች እንደሚያስተላለፍ የተናገሩት ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ የመጀመሪያው አመራሮቹ ለከፈተኛ ማዕረግ የበቁት አስቸጋሪ ፈተናዎችን በጽናት በማለፍ ሀገራችን ኢትዮጵያን በገቡት ቃል ኪዳን መሰረት በትጋት፣ በአርአያነትና በታማኝነት በማገልገላቸው ለመልካም ተግባራቸው የተሰጠ ዕውቅና እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሹመቱ ጀኔራሎቹ የሀገራችንን የብልጽና ጉዞ ለማሳካት እንዲቻል ሰራዊቱን በብቃት በመምራትና አስተማማኝ ሰላም በማረጋገጥ ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን እንደሚያሳይ ፕሬዚዳንቷ አስገንዝበዋል፡፡

ክብርት ፕሬዚደንቷ አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ አለምአቀፍ ትብብርና ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን በመግለጽ፤ ጀኔራል መኮንኖቹ ይህን ከባድ ኃላፊነት በዕውቀትና ክሕሎት ለመፈጸም ተከታታይ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ‹‹በጦርነት ጊዜ ጋሻ፣ በሰላም ጊዜ ደግሞ ትከሻ ሆኖ ሀገሩን የሚደግፍ፣ የሚጠብቅና የሚያኮራ የመከላከያ ሰራዊት ስላለን በእናንተ የምንኮራ መሆኑን ልገልጽላችሁ እፈልጋለሁ›› ካሉ በኋላ፤ ስልጠናውን እና ትጥቁን ከጊዜው ጋር ለማዘመን፣ አኗኗሩንና አደረጃጀቱን፣ ክብሩንና ተልዕኮውን የሚመጥን ለማድረግ የሪፎርም ስራዎች በመስራት ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ አስታውቀዋል፤ ይህ መልካም ስኬት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ጀኔራል አደም መሀመድ በበኩላቸው ሰራዊቱ የተገነባባቸው ህዝባዊ ባህሪያትና የተላበሳቸው እሴቶች ምንጊዜም ውግንናው ለህዝብና ለህዝብ ብቻ በመሆኑ በተሰማራባቸው ቦታዎች ሁሉ የሚፈጽማቸው ግዳጆች  በድል የታጀቡ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ሠራዊቱ ዘመኑ የሚጠይቀውን ሁለገብ ብቃት እንዲላበስ ለማድረግና ዝግጁነቱን ለማጎልበት ያለሰለሱ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውንና ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ እንደሆነ ፤ያስተወሱት ጀኔራል አደም፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሰጡት ብቁ አመራርም አመስግነዋል፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና...
ነሐሴ 26 12 2012 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ነሐሴ 17 12 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ ፣ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል...
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፤ የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር...