በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በኢ... አየር ኃይል ደረጃ ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለሰው ኃብት ልማት ሙያተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ከመከላከያ ሰው ሀብት ዋና መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች 4 ተከታታይ ቀናት በተሰጠው የማጠቃለያ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ተጨማሪ ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት የሥራ መመሪያ የሰጡት የመከላከያ የሰው ኃብት ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ / አጫሉ ሸለመ ናቸው፡፡
ኃላፊው በገለፃቸውም ስለ ሰው ኃብት አመራር ተግባራትና ተግዳሮቶችን ስለ ስራ ምዘናና ስለሚታዩ ችግሮች ስለ እድገት መመሪያዎች ስለሰው ኃብት አመራርና ልማት በመከላከያ ደረጃ ስለሚከናወን ተልዕኮ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም በቂ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ጄኔራል መኮንኑ አክለውም የሰው ኃብት ስራ ሙያዊ ኃላፊነትን የሚጠይቅ የአስተዳደር ስራ መሆኑን ገልፀው ሰውን ለማብቃትና የውጊያ አቅምን ለማሳደግ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ሙያተኞች ተቀናጅተው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
የኢ... አየር ኃይል ዋና አዛዥ / ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው ተቋማዊ ለውጡን ለማፋጠን ስልጠና እንደ አንድ ትልቅ የለውጥ መሣሪያ ተወስዶ በሪፎርሙ እየተሰራበት መሆኑን ገልፀው በምንሰራበት የስራ መስክ ሁሉ በስራ አፈፃፀም ምዘናና በዳታ አያያዝና በመሰል የአስተዳድር ስራዎች የኃላፊነትና የሞራል ተጠያቂነት ሊኖረን ይገባል ብለዋል፡፡
የኢ... አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለሰው ኃብት ልማት / ይታያል ገላው በበኩላቸው እያንዳንዱ አመራርና አባል ከስልጠናው ባገኘነው እውቀት ተቋማዊ ለውጡን ለማሳካት የተሻለ ስራ መስራት ይጠበቅብናል በማለት ስልጠናውን ለሰጡት የመከላከያ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና...
ነሐሴ 26 12 2012 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ነሐሴ 17 12 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ ፣ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል...
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፤ የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር...