የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

ኢንተርፕራይዙ ለከፍተኛ የሰራዊት እና ሲቭል አመራሮች ለስድስት ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ኢታማጆር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፤ እንደገለፁት የኮንስትራክሽን ድርጅቱ እስካሁን ድረስ በግንባታዉ ዘርፍ እጅግ አስቸጋሪ ፣ ፈታኝ በሆኑ መልከአ ምድር እና የአየር ፀባይ ባለባቸዉ የአገራችን አካባቢዎች ጭምር ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በብቃት እና በጥራተ ሰርተዉ በማስረከባችዉ ያላቸዉን አድናቆት እና ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በማስከተልም በአንዳንድ ፐሮጀክቶች ላይ ከደንበኞች የሚነሱ የጥራት እና በወቅቱ አጠናቆ ከማስረከብ አንፃር ክፍተቶች ስላሉ እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ወሳኝ ሚና ስላለዉ በርትታችሁ በንቃት በመሰልጠን መንግስት እና ተቋሙ ከእናንተ የሚጠብቁትን ልማታዊ ስኬት እዉን ልታደርጉት ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

በስልጠናዉ ላይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ጌታቸዉ ኃይለማርያም፣ የኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ደቦ ቱንካ፣ የኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት፣ የግንባታ ግበዓት ማምረቻ ድርጅት እና የዘርፍ እስታፍ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፡-

 

የስልጠናዉን ዓላማ አስመልክቶ ክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ አቶ ጌታቸዉ ኃይለ ማርያም እንደገለፁት ኢንተርፕራይዙ በዕለት ተዕለት ስራዎች ላይ የአመራሩ የማስፈፀም አቅም እና የአሰራር ክፍተት እንዲሁም የክፍያ አሰባሰብ ላይ አንዳንድ ችግሮች መኖራቸዉን ገልፀዋል፡፡

  በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት እንደሃገር  በቢሊዬን ብር ዋጋ ያላቸዉ ዘመናዊ የሰራዊቱ የመኖሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ ቢሮዎች፣ ኮሌጆች፣ የአስፓልት መነንገዶች እና የአዉሮፕላን ማረፊያ ግንባታዎች ያሉን በመሆኑ እነዚህን ግንባታዎች ሃላፊነት፣ ተጠያቂነት እና ግልፀኝነት በተሞላበት መልኩ በጥራት እና በፍጥነት ገንብተዉ በማስረከብ አገራዊ ለዉጡን በማሳለጥ የበኩላቸዉን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ለሰልጣኝ አመራሮቹ አሳስበዋል፡፡

ስልጠናዉ በዋናነት ካተኮረባቸዉ ነጥቦች መካከል የኮንስትራክሽን ፕረጀክት ስራ አመራር፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የስጋት ስራ አመራር፣ የቦርድ አስተዳደር መመሪያ እና የሃብት አስተዳደር የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

ስልጠናዉን የሰጡት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢትዮጲያ ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት እና ከመንግስት የልማት ተቆጣጣሪ ዋና መስሪያ ቤት የመጡ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ናአዉ፡፡

በስልጠናዉ ላይ ሲሳተፉ አግኝተን ካነጋገርናቸዉ አመራሮች መካከል የባህርዳር ፕሮጀክቶች ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዘመን ታደሰ በሰጡት አስተያየት ሁሉም የፕሮጀክት አመራሮች በጋራ ሆነን የዚህን አይነት ስልጠና መዉሰዳችን ከስልጠናዉ ከምናገኘዉ አቅም በተጨማሪ እርስ በእርሳችን ልምድ እና ተሞክሮ የተለዋወጥንበት ስልጠና በመሆኑ ለቀጣይ ስራችን ትልቅ አቅም አግኝተንባል በማለት ገልፀዉ ለቀጣይም የዚህ አይነቱ ስልጠና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

  በተመሳሳይ መልኩ የሸጎሌ የመኖሪያ ቤት እና የመከላከያ ስታፍ ኮሌጅ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይሌ ገብረዋህድ አንደገለፁት በኮንስትራክሽን ስራ ላይ ከዕቅድ እስከ ትግበራ ድረስ በርካታ ተግዳሮቶች ያሉ በመሆኑ እነዚህን ችግሮች እንዴት መቅረፍ እንደምንችል እና ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ቀድመን በመተንበይ አስቀድመን መከላከል የሚያስችለንን እዉቀት ከሰልጠናዉ አግኝተናል ካሉ በኋላ አሁን ወደየስራችን ተመልሰን ያገኘነዉን አቅም ወደ ተግባር መቀየር የሁላችንም ሃላፊነት ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም በስልጠናዉ መዝጊያ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ተወካይ እና የፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮሎኔል ፍሰሃ ዘዉዴ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ስነ-ስረዓት በመኮንኖች ክበብ በተዘጋጀዉ መርሃ ግብር ላይ በእለቱ የክብር እንግዳ ኮሎኔል ፍሰሃ ዘዉዴ እና በመከላከያ መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታዉ አቶ ጌታቸዉ ኃይለ ማርያም አማከኝነት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማትን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት በማስተላለፍ፤ ለአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች  ሰርተፊኬት በመስጠት እና መልካም የስራ ዘመን በመመኘት የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡

    

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
የህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ለሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም የሚያገለግሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በምድር ሃይል ግቢ በመገኘት ለየእዝ አመራሮችና ለመምሪያ ሃላፊዎች ቁልፍ አስረክቧል፡፡