ኮሌጁ ሰልጣኞችን አስመረቀ

 

 

የሜጀር ጄኔራል ሙልጌታ ቡሊ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመደበኛ የስልጠና መረሃ ግብር በተለያዩ የስልጠና ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ሶስት መቶ ዘጠና አምስት የሠራዊት አባላትን አስመርቋል።

በምርቃ ስና-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሜጀር ጄኔራል ሓየሎም አርአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ መኩሪያ፤ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ እየተከነወኑ ከሚገኙ ዘርፈ ብዙ የአቅም ግንባታ ተግባራት ተቋማችን ለትምህርትና ስልጠና ከፍተኛ ትኩረት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው፣ ሠራዊቱ የተሰጠውንና ወደፊት የሚሰጠውን ግዳጅ በአስተማማኝ፣ በብቃትና በላቀ ጀግንነት መፈፀም እንዲችል የተቋሙ ኮሌጆች ዘርፈብዙ ሥራ እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ዋና አዛዡ አያይዞም የሜጀር ጄኔራል ሙልጌታ ቡሊ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተቋሙ በሚያካሄደው የመደበኛ ዘመነዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደት ላይ በልዩ ልዩ ሙያዎች ሠራዊቱን በማሰልጠን የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ እንድሆን አብረርተዋል። ተመራቂዎችም የፈጠሩትን አቅም እንደመነሻ በመውሰድና ተጨማሪ አቅም በመፍጠር ሠራዊቱ ተልዕኮውን በብቃት እንዲፈፅም ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዚሁ ቀን የተገኙት የሜጀር ጄኔራል ሙልጌታ ቡሊ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥ ኮሌኔል ብረሀነ ተክለ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ የተሰጠውን የማሰልጠን ተልዕኮ ተቀብሎ የቋማችንን ፍላጎት መነሻ በማድረግ መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የስልጠና ፕሮግራሞች በመንደፍ ከተለያዩ የሠራዊት ክፍሎች በርከታ አባላትን በማሰልጠን የተቋሙን የሰለጠና የሰው ኃይል እጥረት በመፍታት የበኩሉን አስተዋፆ ሲያደርግ መቆየቱን በማስታወስ፤ በአሁኑ ጊዜም ኮሌጁ ለበርካታ ዓመታት ያካበታውን ልምድ በመጠቀምና አዳድስ የስልጠና ፕሮግራሞችን በመጨመር የተሰጠውን የማሰልጠን ግዳጅ በተሻለ ብቃት እየፈፀመ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል ሻምባል ባሻ ሰለሞን ሽመልስና ሻምባል ባሻ መስታውት ቡሹላ በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት፤ ኮሌጁ በተግባር የተደገፈ ስልጠና በመስጠት ብቁ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል። ተመራቂዎቹ በቀጣይም ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በሚሄዱበት ክፍል በሙሉ ተነሳሽነት እንደሚያገለግሉ ገልፀዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
የህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ለሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም የሚያገለግሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በምድር ሃይል ግቢ በመገኘት ለየእዝ አመራሮችና ለመምሪያ ሃላፊዎች ቁልፍ አስረክቧል፡፡