የምስራቅ አፍሪካ የተጠንቀቅ ሀይል አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ

የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ሀይል /EASF/ አዲስ አበባ በሚገኘዉ ዋና መስሪያ ቤት ለአራት ተከታታይ ቀናት  አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ፡፡

በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ፍሰሃ ወልደ ሰንበት ባሰሙት ንግግር እንደገለፁት አሁን ካለዉ የአለም ነባራዊ ሁኔታ በርካታ ተግዳሮቶች ያሉበት ወቅት ላይ የምንገኝ በመሆኑ ፤ እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት እና አፍሪካ ህብረት ስር በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ በምናደርገዉ ተሳትፎ ለቀጠናዉ  ሃገራት፣ ለአህጉሩ እንዲሁም ለአለም ሰላምን የማረጋገጥ ተልዕኮ ወቅቱ የሚፈልገዉን ፈጣን፣ ተጣጣፊ እና ሃላፊነት የተሞላበት ምላሽ መስጠት እንድንችል የሰዉ ሃይል መመሪያ ደንቡን ማሻሻሉ አስፈላጊ እና ወቅታዊ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ስብሰባዉ አዲስ አበባ ላይ መካሄዱ እንደ ሃገር ልምድ እና ተሞክሮ እንድናገኝ ይጠቅመናል ካሉ በኋላ ለተሰብሳቢዎች ዉጤታማ የዉይይት ጊዜ እና መልካም የአዲስ አበባ ቆታን በመመኘት ንግግረቸዉን  ቋጭተዋል ፡፡

 በማስከተልም በዕለቱ የፕሮግራም መክፈቻ ስነ-ስረዓት ላይ የተገኙት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱላሂ ኦማር ባሰሙት ንግግር እንደገለፁት አሁን ካለዉ ተጨባጭ የዓለማችን ሁኔታ በመነሳት  ከዚህ በፊት የነበረዉን የድርጅቱን የሰዉ ሃይል መመሪያ፣ ደንብ እና ፖሊሲዎች ማሻሻል እና ማዳበር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ   ድርጅቱን በመሰረቱት አባል ሃገራት የጋራ ስብሰባ መጠራቱን በመግለፅ  በዚህም የተሳካ ዉይይት በማከሄድ ዉጤታማ የጋራ ዉሳኔ ላይ እነደሚደርሱ ያላቸዉን ፅኑ እምነት ገልፀዉ የዉይይቱን  አጀንዳዎች ለተሳታፊዎች በማስተዋወቅ ስብሰባዉን አስጀምረዋል፡፡

 በስብሰባዉ ላይ የተቋሙ  ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱላሂ ኦማር ቦህን ጨምሮ ፣ የድርጅቱ የሃይል አዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ሳላዲን ኦስማን ሚርግሃኒ፣ የሎጀስቲክስ ዋና አዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ጎድዊን ካሩጋባ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር ምዌሲጌ ካሳኢጃ አዶልፍ ፣ የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ፍሰሃ ወልደ ሰንበት፣ ከአባል ሃገራት የመጡ የህግ ፣ የሰብዓዊ መብት እና የሰዉ ሃይል አስተዳደር  ከፍተኛ ኤክስፐርቶች፣ የድጋፍ ሰጪ እና ተባባሪ ሃገራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንዶች ተገኝተዋል፡፡

ለአራት ቀናት በቆየዉ ስብሰባ አባል ሃገራቱ በበርካታ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን በመጨረሻም የተለያዩ መመሪያወችን፣ ደንቦችን እና ፖሊሲዎችን ለማሻሻል ዉሳኔ ላይ መድረሳቸዉ ተገልጿል፡፡ የተጠንቀቅ ሀይሉ ተጠሪነቱ ለአፍሪካ ህብረት ሲሆን የተቋቋመበት ዋነኛ ዓላማ እና ሃላፊነትም በምስራቅ አፍሪካ ሰላም እና ፀጥታን ማስፈን ነዉ፡፡

የድርጅቱ /EASF/ አባል ሃገራት አስር ሲሆኑ እነሱም ኢትዮጵያ ፣ ብሩንዲ ፣ ኮሞሮስ ፣ ጅቡቲ ፣ ኬንያ ፣ ሩዋንዳ ፣ ሶማሊያ ፣ ሱዳን ፣ኡጋንዳ እና ሲሼልስ ናቸዉ ፡፡ የድርጅቱ ዋና ፅህፈት ቤት መገኛም አዲስ አበባ ነዉ፡፡

ድርጅቱ በርካታ ድጋፍ ሰጪ እና አጋር አገሮች ያሉት ሲሆን ከእነሱም ዉስጥ አሜሪካ፣ አዉስተራሊያ፣ ካናዳ፣ ቤልጂየም፣ ቱርክ ፣ ጃፓን፣ ጀርመን፣  ፈረንሳይ፣  ቻይና እና ኖርዌ …ተጠቃሽ  ናቸዉ፡፡

በመጨረሻም  የድርጅቱን  15ኛ  አመት  የምስረታ  በዓል  በማክበር  ስብሰባዉ  ተጠናቋል ፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
የህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ለሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም የሚያገለግሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በምድር ሃይል ግቢ በመገኘት ለየእዝ አመራሮችና ለመምሪያ ሃላፊዎች ቁልፍ አስረክቧል፡፡