የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ሠልጣኞችን አስመረቀ

የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታን ለማፋጠንና ተቋ ማዊ ሪፎርሙ ግቡን እንዲመታ ለተከታ ታይ ወራት ያሰለጠናቸውን አዲስ የኮማንዶ አባላት አስመረቀ፡፡       

ሰሞኑን በተከናወነው በዚሁ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የክፍሉ መለያ የሆነውን ቀይ ቦኔት ለዕለቱ ተመራቂ የኮማንዶ አባላት ካለበሱ በኋላ የመ መሪያ ንግግር ያደረጉት የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ክቡር ሜጀር ጄኔራል ሹማ አብደታ ናቸው፡፡

ሜ/ጄኔራሉ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር ተመራቂዎች ትላንት በህዝብ ውስጥ ሆነው የለውጡ ዋና አራማጅ እንደነበሩ በማስታወስ፣ ወደ መከላከያ ሠራዊቱ በመቀላቀል መስዋዕ ትነት ጭምር ለከፈሉለት ለውጥ ቀጣይነትና ለህገ-መንግስቱ ዘብ በመቆማቸው ታላቅ ኩራት ሊሰማቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

´ኮማንዶ ለልዩ ጥቅም የቆመ ኃይል ሳይሆን፣ ለሀገርና ለህዝቦች የጋራ ጥቅም የተሰለፈ ኃይል ነውª ያሉት ሜጀር ጄኔራል ሹማ፣ በአሁኑ ወቅት በሀገርና በህዝብ ላይ የተጋረጠውን አደጋ በመጋፈጥ ማንኛውንም ፈተናዎች የሚቀበል፣ ታጋሽ፣ ለሀገርና ለህ ዝቡ አስፈላጊውን መስዋዕትነት የሚከፍል ኃይል መሆኑን   ገልፀዋል፡፡

ሜ/ጄኔራል ሹማ አክለ ውም የዕለቱ ተመራቂዎች ከነ ባሩ ኃይል ጋር በመቀላቀል ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ጥቅ ምና ደህንነት የትኛውንም ፈተናዎች በፅናት በመጋፈጥ ለህገ -መንግስታዊ ተልዕኮዎች አስፈላጊውን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አሳ ስበዋል፡፡

የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ ኮሎኔል ኃይለስላሴ ተስፋ ሚካ ኤል በበኩላቸው ባቀረቡት የስልጠና ሪፖርት፣ ተመራቂ የኮማንዶ አባላት እጅግ ፈታኝ፣ ውስብስብና እልህ አስጨራሽ የሆነውን የኮማንዶ ስልጠና በብቃት ማጠናቀቃቸውን በመግለፅ በቀጣይ ለሚሰጣቸው ሀገራዊ ግዳጆች አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎችን በመቋቋም በብቃት መፈ ፀም የሚያስችላቸውን አቅም መፍጠራቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡

የማሰልጠኛ ማዕከሉ አሰልጣኞችም በሰ ጡት አስተያየት ተመራቂዎቹ ስልጠናውን ለመቀበል የነበራቸውን ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት በማድነቅ በቀጣይም ተተኪ ኃይል የማፍራት ሥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረ ጋግጠዋል፡፡

የኮማንዶ አባል በመሆን ለሀገራዊ የጋራ ዓላማ በመቆማቸው ትልቅ የደስታ ስሜት እንደፈጠረላቸው የተናገሩት የዕለቱ ተመራ ቂዎች በበኩላቸው የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት በታማኝነትና በጀግንነት ለመወጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

 በዕለቱ በዚሁ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከተገኙት የተመራቂ አባላት ቤተሰቦች መካከል አቶ ሃጅ አህመድ ሳሊያና እና ወ/ሮ ሳኒያ ሰይድ በበኩላቸው ልጆቻቸውን ለማስመረቅ በፕሮግራሙ ላይ መገኘታቸው እንዳስደሰታቸውና ለወደፊቱም ህዝባችን ለሠራዊቱ ያለውን ከፍተኛ ክብር ይበልጥ በማሳደግ ከጎናቸው መቆም ይገባል በማለት አስተያያታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ዘገበው የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሠልጠኛ ማዕከል ሪፖር ተር ሻምበል አብዱራህማን ሀሰን ነው፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!