በሰሜን አየር ምድብ የቤተሰብ ቀን ተከበረ

ከአየር ኃይል ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር

በሰሜን አየር ምድብ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የቤተሰብ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በድ ምቀት ተከበረ።

መቀሌ በሚገኘው የአየር ምድቡ መኖሪያ ካምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከበረው የቤተሰብ ቀን ላይ የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና እና የኢፌዴሪ አየርኃይል አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተገኝተዋል።

በዕለቱ በተካሄደው የቤተሰብ ቀን ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ይልማ፤ በ2011 በጀት ዓመት በተቋማችን የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለማሳካት ወትሮ ዝግጁነታችንን ይበልጥ ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ´ሠራዊቱ ሀገር እንጂ ብሄር የለውምª በሚል መርህ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወገንተኝነት የፀዳ ህገ-መንግሥቱንና ህገ -መንግሥታዊ ስርዓቱን የሚጠብቅ ነው ብለዋል።

መከላከያ አራተኛው ትውልድ የሚከ ተለውን የውጊያ ጥበብ መታጠቅ የሚችል ዘመናዊ መደበኛ ሠራዊት የመገንባት ሥራን አጠናክሮ የቀጠለበት ዓመት ነው ብለዋል።

ብርጋዲየ ጄኔራል ይልማ አክለውም የ2011 በጀት ዓመት ከስኬቶቻችን በተቃራኒ በጽንፈኛ ኃይሎች አማካኝነት ጀግኖች መሪ ዎቻችንን ያጣንበት ከመሆኑም በተጨማሪ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በጽናት የመሻገር አቅም እንዳለን ያስመሰከርንበት ዓመት መሆኑን ገልፀዋል።

የቤተሰብ ቀን በአየር ምድቡ መከበሩ የሠራዊቱንና ቤተሰቡን ግንኙነት ከማጠናከርና የእርስ በርስ ትውውቅ መድረክ ከመፈጠር በተጨማሪ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት በትምህርታቸው ጠንክረውና በሥነ-  ምግባር ታንፀው መልካም ዜጋ ሆነው እንዲያድጉ የሚያደርግ ከሠራዊታችን የሚጠበቅ በጎ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።

የሰሜን አየር ምድብ አዛዥ ሌተና ኮሎኔል ወንዱ ኬዳ በበኩላቸው አየር ምድቡ በ2011 በጀት ዓመት በመከላከያም ብሎም በአየር ኃይል ደረጃ የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም ለማሳካት ከምድቡ የግዳጅ ሁኔታ ጋር በማስተሳሰር ከአደረጃጀትና ካለው ኃይል ምደባ ጀምሮ ሰፋፊ የለውጥ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በሰሜን አየር ምድብ በተካሄደው የቤተሰብ ቀን ላይ በ2011 በጀት ዓመት የላቀ አስተዋኦ ለነበራቸው የምድቡ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች እንዲሁም በአካዳሚ ትምህርታቸው ከየክፍሉ 1ኛ ለወጡ የሠራዊቱ አባላትና የሠራዊቱ ልጆች ከዕለቱ የክብር እንግዳ ከሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና እና ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እንዲሁም ከአየር ኃይል ኮማንድ እጅ የተዘጋጀላቸውን ልዩ ልዩ ሽልማቶችንና የዕውቅና የምስክር ወረቀት  ተቀብለዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
የህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ለሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም የሚያገለግሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በምድር ሃይል ግቢ በመገኘት ለየእዝ አመራሮችና ለመምሪያ ሃላፊዎች ቁልፍ አስረክቧል፡፡