መከላከያ በእስር ላይ ለነበሩ የሠራዊቱ አባላት ይቅርታ አደረገ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በተቋሙ በህግ ጥላ ሥር የነበሩ የህግ ታራሚ የሠራዊት አባላትን በይቅርታ እንዲፈቱ አደረገ።

የመከላከያ ወታደራዊ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ፍሰሀ ዋሴ ለመከላከያ ሚዲያ እንደገለፁት፤ ባገባደድነው 2011 ዓ.ም በዳይሬክተሩና በይቅርታ ቦርዱ አማካኝነት ለ255 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስ ታውሰው ዘንድሮም ለ2012 አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በህገ-መንግሥቱ አን ቀጽ 71 ንዑስ አንቀፍ 7 መሰረት ለ80 የህግ ታራሚ አባላት ይቅርታ መደረጉን አስታው ቀዋል።

የመከላከያ ወታደራዊ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት ዋና ዓላማ ወንጀልን መከላከል ነው ያሉት ኮሎኔል ፍሰሀ፤ በህገ- መንግሥቱ የተቀ መጠውን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ የታራሚ ዎችን አያያዝና አስተዳደራዊ ሁኔታዎችን በመከታተል መፍትሄ በመስጠት ታራሚው ወንጀልን እንዲፀየፍና እንዲጠላ የሚያደርግ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ተሰርቷል ብለዋል።

በመከላከያ ወታደራዊ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት የማዕከል ማረሚያ ቤት ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል አጽብሃ አብርሃ በበኩላቸው ከእስር የተፈቱት ታራሚዎች 1/3 የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁና ከፈፀሙት የወንጀል ድርጊት ትምህርት በመውሰድ የሥነ - ምግባር ለውጥ ያመጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

መኮንኑ አያይዘውም የአባላቱ የእስር አያያዝ አስተዳደራዊ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን ባከበረ መልኩ እንደነበር ገል ፅው፤ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ከግንባታ ትምህርት ጀምሮ የህግ ግንዛቤ ስልጠና ወስ ደዋል ብለዋል።

በአዲሱ ዓመት ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል ፶ አለቃ ጁነዲን አብድል ጀባር እና ወ/ር መሰረት ታደ በሰጡት አስ ተያየት በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የነበ ራቸውን አያያዝ መልካም መሆኑን ገልፀው፤  በቆይታቸው ከተፈቱበት ጊዜ ጀምሮ ወድ አሃዱዋቸው ሲመልሱ አባላቱ ከማንኛውም የወንጀል ድርጊት እና ከሥነ - ምግባር ግድፈት እንዲጠብቁ እንመክራለን ብለዋል።

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
የህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ለሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም የሚያገለግሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በምድር ሃይል ግቢ በመገኘት ለየእዝ አመራሮችና ለመምሪያ ሃላፊዎች ቁልፍ አስረክቧል፡፡