መከላከያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚሳተፉ አትሌቶች አሸኛኘት አደረገ

የመከላከያ ስፖርት ክለብ ዳይሬክቶሬት በ16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና  ሀገራቸውን ወክለው ለሚሳተፉ አትሌቶች አሸኛኘት አደረገ።

በአሸኛኘት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የመከላከያ ስፖርት ክለብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ደረጀ መንግሥቱ ክለቡ በልዩ ልዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች በብቃት በመሳተፍ የሀገራችንን የአትሌቲክስ ስፖርት ዕድገት ለማገዝ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

የመከላከያ ስፖርት ክለብ የአትሌቲክስ፣ የመረብና እጅ ኳስ ኃላፊ ኮሎኔል ንጉሴ አየለ በበኩላቸው፤ ተቋሙ በእንግሊዝ ለንደን በሚካሄደው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በብሄራዊ ደረጃ ከተመረጡ 40 አትሌቶች መካከል አምስት ማስመረጡን አስታውቀዋል።

ኃላፊው እንዳስታወቁት ሻለቃ አትሌት የማነ ፀጋዬ በማራቶን፣ ፶ አለቃ እቴነሽ ዲሮ በ3ሺህ ሜትር መሰናክል፣ ፲ አለቃ ሙክታር እንድሪስ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ፣ ም/፲አለቃ ታፈሰ ሰቦቃ በ3ሺህ ሜትር መሰናክል እንዲሁም ወታደር አስካለ ትክሳ በእርምጃ ውድድር ይሳተፋሉ፤ ሁሉም አትሌቶች ተገቢውን ልምምድ እንዳደረጉም ገልጸዋል።

ሀገራቸውን ወክለው በ16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሚወዳደሩ አትሌቶች መካከል ሻለቃ የማነ ፀጋዬ፣ ፲ አለቃ ሙክታር እድሪስና ወታደር አስካለ ትክሳ በሰጡን አስተያየት፤ “ተቋማችን ብሎም ሀገራችን የሰጡንን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት በአካልም ሆነ በሥነ-ልቦና ተዘጋጅተናል” ብለዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በጀኔራሎቹ ሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በጀኔራሎቹ ሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
ኢትዮጵያውያን ሁሉ በተፈጥሮ ወታደሮች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ደግሞ የተፈጥሮ ወታደርነትን ከዘመናዊ ስልጠናና ከዲስፕሊን ጋር ያዋሀዱ ምርጦች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ይህ ነው...
ታህሳስ 26 04 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ደረጃ ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለሰው ኃብት ልማት ሙያተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ከመከላከያ ሰው ሀብት ዋና መምሪያ...
ጥር 03 05 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ በጦር ሃይሎች ከምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ፡፡