የሠራዊቱ ክፍሎች የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ

በኢፌዴሪ አየር ኃይል ማዕከላዊ አየር ምድብ በረራ ክንፉ፤ ስኳድሮንና ልዩ ልዩ ክፍሎች የ2011 ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ፡፡

በዓመታዊ ግምገማው ማጠቃለያ  ላይ በመገኘት በሥራ አፈጻጸማቸው ውጤታማ ለነበሩ ክፍሎችና አባላት ሽልማት በመስጠት የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እንደተናገሩት፤ በበጀት ዓመቱ የተጀመረውን የሪፎርም ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም በየድርሻው የተሰጠውን ኃላፊነትና ግዳጅ በብቃት መወጣት በመቻሉ ሂደቱ ዉጤት እያስገኘ ይገኛል፡፡

በቀጣይም ተቋማችን የጀመረውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል አዳዲስ አሰራሮችን በመ ፍጠርና ሃሳቦችን በማመንጨት በተለይም ተሸላሚ የሄሊኮፕተርና የትራንስፖርት አውሮፕላን ክንፍ ክፍሎች ጥንካሬያቸውን በማስቀጠል ለሌሎች ተሞክሮ ማስተላለፍ እን ዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ዘገባው የአየር ምድቡ ሪፖርተር የጁ/ኤክ ሜሮን ጌታነህ ነው፡፡

 ይህ በእንዲህ እንዳለ የ2ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ኮማንድና ብርጌድ አመራሮች የ2011 በጀት ዓመት ግምገማ አካሄዱ፡፡

የ2ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን እንደገለጹት ™ግምገማው መንግስትና ተቋማችን የሰጡንን ሀገራዊና ዓለማቀፋዊ ግዳጅ በብቃት ለመፈጸምና ውስጣዊ አንድነታችንን ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ስህተቶች ካሉም ለወደፊት እንዳይከሰቱ ያግዛል∫ ማለታቸውን የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፶ አለቃ ሀሰን ጀማል ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በሰሜን ዕዝ 31ኛ አድዋ ክፍለ ጦር የ2011 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡

የሥራ አፈጻጸም ግምገማውን የመሩት የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ከበደ ፍቃዱ እንደገለጹት፤ የግምገማው ዋና ዓላማ በአዲሱ በጀት ዓመት የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባባት ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡ ዘገባው የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፲ አለቃ ኤፍሬም አድማሱ ነው፡፡

በተያያዘ ዜና በሰሜን ዕዝ ወጋገን 7ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ሲያካሄድ የቆየው ዓመታዊ የሥራ አፈጻጻም ግምገማ ተጠናቀቀ፡፡

የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጉዑሽ ገብረ በግምገማው ማጠቃለያ፤ ክፍለ ጦሩ በበጀት ዓመቱ ህዝብና መንግሥት የሰጡትን ህገ-መንግሥታዊ  አደራ በብቃት መወጣት እንዲችል ሰፋፊ የወታደራዊ አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን አብራርተው የተጀመረው ተቋማዊ የለውጥ ጉዞ ለማሳካትም በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲሱን አደረጃጀት እውን በማድረግ አደረጃጀቱን የሚመጥኑ ሥልጠናዎች በመስጠት የሠራዊቱን አቅም ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል ሲል የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር መ/፶ አለቃ ፍቅሩ ከበደ ዘግቧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ዕዝ የ4ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የ2011 ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡

የ4ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቢሰጥ ጌታሁን የዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ዓላማ በሚቀጥለው በጀት ዓመት ክፍለ ጦሩ ሁለንተናዊ ጥንካሬውን አስጠብቆ ለማስቀጠል መሆኑን ጠቁመው አመራሩና አባሉም የተሻለ ስራ መስራት እንዳለበት መናገራቸውን የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ሻምበል አበራ ደበሌ ያደረሰን ዘገባ ያስረዳል፡፡

በተያያዘ ዜና 13ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ በኪስማዩ የተወጣው ግዳጅ አፈጻጸም ውጤታማ እንደነበር ገለጸ፡፡

የ13ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሊጋዝ ገብሬ እንደተናገሩት፤ የሻለቃዋ አባላት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውጤታማ ግዳጅ መፈጸማቸውን አስታውሰው፤ በጎረቤት ሶማሊያ አመራሩና አባላቱ  አስተማማኝ ወታደራዊ ብቃት እና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነት በመላበስ በተወጡት ግዳጅ በወገን ላይ ጉዳት ለማድረስ የተንቀሳቀሰውን የጠላት ኃይል ዕቅድ ማክሸፍ መቻላቸውን ተናግረዋል ሲል የሻለቃዋ ሪፖርተር ፶ አለቃ ጌታቸው ተስፋዬ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በሰሜን ዕዝ በ20ኛ ቃሉ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ  የዓመቱ ግዳጅ አፈጻጸም አበረታች እንደነበር ተገለጸ፡፡

የብርጌዱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አምባቸው ጫኔ እንዳሉት፤ የሠራዊቱ ወትሮ ዝግጁነትና  ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ ይበልጥ ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን መግለጻቸውን የብርጌዱ ሪፖርተር ፶ አለቃ አረቡ ሰይድ ያደረሰን ዘገባ ያስረዳል፡፡

በሌላ ዜና የ24ኛ ክፍለጦር የ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ።

የምዕራብ ዕዝ  ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ብርጋዲየር ጄኔራል አሰፋ ቸኮል እንደገለፁት ባሳለፍነው በጀት ዓመት የክፍለጦሩ ሠራዊት አባላት በርካታ ግዳጆችን በብቃት ተወጥተዋል። የክፍለጦሩ አመራርና አባላት ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍፁም ቁርጠኝነትን ተላብሰውና ተግተው በመስራት ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ የበለጠ ውጤት ማምጣት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት አገልግሎት ኮሎኔል ኑርዬ አስፋው በበኩላቸው፤ ክፍለጦሩ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ አስተማማኝ ሠላም ለማረጋገጥ ሠራዊቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ቁመናና የሥነ - ልቦናዊ ዝግጁነት  እንዳለው ተናግረዋል ሲል የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፶ አለቃ ሰማኸኝ ጥላሁን ያደረስን ዜና ያስረዳል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ዕዝ 13ኛ ክፍለጦር የሠራዊት አባላት የግዳጅ አፈፃፀም ግምገማ አካሄዱ።

የተካሄደውን ግምገማ አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ የሰው ሀብት ልማት ኮሎኔል ሶፊያን ሼህ መሀመድ የ2011 ዓ.ም የግምገማ ትኩረት ክፍለ ጦሩ በተሰማራባቸው ሀገራዊ ግዳጆች እና በጎረቤት ሀገር በሠላም ማስከበር ተልዕኮዎች በተደረጉ ስምሪቶች የተገኙ ውጤቶችን ሠራዊቱ እንዲገነዘበው በማድረግ የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ብለዋል።

ምክትል አዛዡ አክለውም ግምገማው የተስተዋሉ ክፍተቶቻችንን ፈጥኖ ለማስተካከል እና ጥንካሬን አጎልብቶ በመቀጠል ለሚሰጡን ግዳጆች ዝግጁ ከማድረግ አኳያ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል ያለው የ13ኛ ክፍለጦር ሪፖርተር ፶አለቃ ተስፋዬ ያረጋል ነው።

በተያያዘ ዜና በደቡብ ዕዝ 21ኛ ክፍለ ጦር የ4ኛ ድጋፍ ሰጪ ብርጌድ የ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

በግምገማው  ማጠቃላያ ላይ የተገኙት የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል አብረሃም ሞሲሳ የሠራዊት ክፍሉ በአሰራር እና መመሪያ መስራት የሚያስችሉ ተከታታይ የግንባታ ተግባራት በማከናወን ለግዳጅ ብቁ የሆነ ሠራዊት በማፍራት በዓመቱ ውስጥ የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱ መሆ ናቸውን ገልፀዋል።

የ214ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል የሽዋስ በበኩላቸው በሀገራዊ ለውጥ እና በመከላከያ ሪፎርም ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር በአስተሳሰብ፣ በመሳሪያ አጠቃቃምና በወታደራዊ ቁመና ዝግጁነት በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን የ214ኛ ብርጌድ ሪፖርተር ም/፲አለቃ ኡመር ታመነ ዘግቧል።

በሌላ በኩል በሰሜን ዕዝ የ7ኛ ውጋገን ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አየር መቃወሚያ ሻለቃ የ2011 ዓ.ም የበጀት ዓመት ማጠቃለያ ግምገማ አካሄደ።

የሁሉም ሻምበሎች እና የሻለቃ ስታፍ መምሪያ አባላት በተገኙበት የማጠቃለያ ግምገማ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሻለቃዋ ዋና አዛዥ ሌተና ኮሎኔል ደሳለኝ ወልድአብዝጊ እንደገለፁት በዓመቱ የሠራዊቱን አደረጃጀት በአዲስ መልክ ለማስተካከል የሚያ ግዙ የመኖሪያ ቤት ግንባታዎችን ጨምሮ ዝግ ጁነቱን ለማጠናከር የሚያግዙ  ስልጠናዎች ተሰጥተዋል።

ዋና አዛዡ ሠራዊቱ በሚወጣው ግዳጅ ላይ ግልጽነት እንዲኖረው በመደረጉ  ሠላምን በአስተማማኝ ማረጋገጥ የሚያስችል ብቃት ላይ እንዲገኝ መቻሉን የሻለቃዋ ሪፖርተር ፲አለቃ አስናቀ አበበ ያደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

በተያያዘ ዜና የምስራቅ ዕዝ ሴት የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች የዓመቱን የስራ ግምገማ አካሄዱ።

የምስራቅ ዕዝ የሴቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ተወካይ ሻለቃ ወርቄ ዘውዱ በግምገማው ላይ  ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በዓመቱ ውስጥ በሴቶች አደረጃጀት እና በሴቶች ተሳትፎ የተሻለ ስራ መሰራቱን ጠቁመው ጠንካራ ጎኑን በማስቀጠል ክፍተቶችንም ዳግም በመ ሙላት በቀጣይ ውጤታማ ስራ እንደሚሰራ መግለፃቸውን የዕዙ ሪፖርተር መ/ወ/ደጀኔ አሰፋ ዘግቧል።


ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!