የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተገለጸ

የመከላከያ ኮንስተራክሽን ኢንተርፕራይዝ  በ2011 የበጀት አመት በርካታ ዉጤታማ ስራዎች ማከናወኑ ተገልጿል፡፡

ሰሞኑን በኢንተርፕራይዙ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው የበጀት አመቱ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት ላይ የተገኙት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም እንደገለፁት በበጀት አመቱ በዲዛይንና በማማከር ገልግሎት ፣ በህንፃና መንገድ ግንባታ ዘርፍ በርካታ ዉጤታማ ስራዎች መሰራታቸዉን ገልፀዋል፡፡

ሚንስትር ድኤታው አቶ ጌታቸው በ2011 የበጀት አመት ሪፖርት ላይ ማብራሪያ እና ማጠቃልያ የሰጡ ሲሆን  በተለይ ከገቢ አሰባሰብ ፣የተያዙ ፐሮጀክቶችን በወቅቱ ከማጠናቀቅ፣ መልካም አስተዳደርን ከማስፈንና የሴቶችን ሁልንተናዊ ተጠቃሚንት ከማረጋገጥ ረገድ ክፍተት ያለብን በመሆኑ ለቀጣይ የተሻለ ስራ ምስራት ይጠበቅብናል በማለት ተናግረዋል፡፡

በማስከተልም  የ2012 የበጀት አመት መሪ የስራ እቅድ ላይ ገለፃ በማድረግ በበጀት አመቱ ያሉብንን የማስፈፀም አቅም ዉስንነቶችን ፈጥነን በመፍታት ከሃያ(20) በላይ የሚሆኑ የተያዙ ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለተጠቃሚ ክፍሎች ማስረከብ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ለዚህም ሁሉም አመራርና ሰራተኛ ለሊትና ቀን ስርተን አቅዳችንን ልናሳካ እና የሰራዊታችንና የህዝባችን አለኝታ መሆናችንን በተግባር ልናረጋግጥ ይገባናል በማለት አሳስበዋል፡፡

የኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ደቦ ቱንካ የ2011 በጀት አመትን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ዋና ስራ አስኪያጁ እንደተናገሩት

በበጀት አመቱ ከተሰሩ ስራዎች ዉስጥ የዲዛይንና የማማከር አገልግሎት፤ የግንባታ እቃዎች አቅርቦት እንዲሁም የህንጻና የመንገድ ግንባታ ስራዎች፤ መልካም አስተዳደርን የማስፈን ፤ሙስናና ብልሹ አሰራርን የመከላከል፤ የስራ እድል ፈጠራና የሰው ሃይልን የማብቃት ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም የየክፍሉ ስራ አስኪያጆች የክፍላቻዉን የ2011 የበጀት አመት የስራ ክንዉን ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በሪፖርቱ ላይ ከቀረቡት ነጥቦች ዉስጥ በኢንተረፕራይዙ እና አህት ድርጅቶች ከተሰሩት በርካታ ስራዎች ዉስጥ በተለይ በመንገድና ህንፃ ግንባታ በመላዉ የአገራችን ክፍሎች በርካታ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመዉሰድ እና በወቅቱ ገንብቶ በማስረከብ ዉጤታማ ስራ መስራታቸዉን ገልፀዋል፡፡

አመራሮቹ አያይዘዉም በስራ ወቅት በርካታ ተግዳሮቶች እንደነበሩና እነሱንም ተጋፍጠዉ ዉጤታማ ስራ መስራታቸውን ገልፀው ከገጠሙን ችግሮች ተምረን ለቀጣይ ስራችን ትልቅ አቅም ፈጥረንባቸዋል፡፡ ከዚህም በመነሳት ለ2012 የበጀት አመት በተቀመጠው እቅድ መሰረት የተሸለና ዉጤታማ ስራ ለመስራት የተቻለንን ሁሉ እነደርጋለን በማለት ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም መላው የኢንተርፕራይዙ አመራሮችና ሰራተኞች የተሳተፉበትና በቅርቡ ለተሰዉት አመራሮች መታሰብያ የሚሆን የችግኝ ተከላ  እና የተለያዩ የፕሮጀክቶች ጉብኝት በማካሄድ የእለቱን ፐሮግራም አጠናቀዋል፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!