ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።

ኮሌጁ የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት በየጊዜው ጥናትና ምርምሮችን ያካሄዳል። በዘንድሮው አመትም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እንድሁም ኮሌጆች ከተወጣጡ ሙሁራን ጋር ሀገር አቀፍ ምርምር  ኮንፈረንስን በኮሌጁ ተካሄዷል። የእለቱ የክብር እንግደ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ  አዛዥ ብርጋዴር  ጄኔራል ዳዊት ወልደሰንበት እንደገለፁት ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አዲስ ቴክኖሎጂ በሚልየ ትኩረት አቅጣጫ በርካታ ጥናትና ምርምር እያካሄደ ይገኛል ብለዋል። እንደ ጀነራል መኮንኑ ገለፀ የኮሌጁ ጥናትና ምርምር የሠራዊቱን ተልዕኮ አፋፃፀም ጉልህ ከማድረጉም በላይ ለሀገሪቱ የኢንዱስትሪ እድገት ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።

በዚሁ ኮንፈረንስ ላይ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ አካዳሚክ ዲን ሌተነል ኮሎኔል ዶክተር እስክንድር አንተነህ እንደገለፁት ኢንጂነሪንግ ኮሌጁ በየጊዜው ጥነትና ምርምሮችን እንደሚያደርግ ገልፀው፣ ጥነትና ምርምሮችን ማካሄድም በሀገሪቱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች በቅርበት እንዲሰሩ ያግዛል ብለዋል።

ሌላኛዉ  የኮሌጅ ተማሪ ምክትል መቶ አለቃ ረብራ እንድሪስ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ማስተርስ ተማሪ እንደገለፀው ኮሌጁ ተማሪዎች በድስፒሊን ታንፀው እንዲወጡ ከማስቻሉም በላይ የተለያዩ ኮንፈረንሶችንና ስልጣናዎችን በማዘጋጀት በየጊዜው ተማሪዎችን ብቁ እያደረገ ይገኛል ብሏል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በ1992 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ኮሌጁ ከተቋቋመ ጀምሮ በየወቅቱ ከሚመጡ ቴክኖሎጂዎች አብሮ የሚጓዝ የሰው ኃይልን በየጊዜው እያፈራ ይገኘል።

በመጨረሻም የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች የችግኝ ተከላ ሥነ-ሥረዓት አካሄደዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!