የሀገር መከላከያ ኢንስፔክተር ጀኔራል ቢሮ የኢንስፔክሽን እና ሴፍቲ ስልጠና ሰጠ

 

 የሀገር መከላከያ ኢንስፔክተር ጀኔራል ቢሮ የኢንስፔክሽን እና ሴፍቲ ስልጠና ሰጠ

 

የመከላከያ ተቋም ዘመናዊ ሠራዊት ለመገንባት በየጊዜው የተለያዩ ስልጠናወችን እየሰጠ ይገኛል። በዘንድሮው አመትም ከተለያዩ ዕዞች፣ ክፍለ ጦሮች እንዲሁም እስታፍ አመራሮች ለተወጣጡ አከላት የኢንስፔክሽን እና ሴፍቲ ስልጠና ለተከታታይ አምስት ቀናት ተሰጥቷል።

በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ኢንስፔክተር ጀኔራል ቢሮ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም እንደገለፁት ተቋሙ ሪፎርሙን መሰረት አድርጐ የተለያዩ ስልጠናወችን እየሰጠ ይገኛል። በዘንድሮው አመትም ከተለያዩ ዕዞች፣ ክፍለ ጦሮች እንዲሁም እስታፍ አመራሮች ስለ የኢንስፔክሽን እና ሴፍቲ ስልጠና እንደተሰጠ በማብራራት፣ የስልጠናው አለማም የሠራዊቱን የውጊያ አቅም ለማጎልበትና በተቋሙ የሀብት አጠቃቀም ስረዓትን ለማሰስ እንዲሁም ሠራዊቱ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃትና በታማኝነት እንዲወጣና በተቋሙ የአሰራር ግልፀኝነት እንዲኖር የማስገንዘብ ስልጠና ነው ብለዋል። አያይዘውም ሜጀር ጀኔራሉ በአሁኑ ጊዜ በሁሉም የተቋሙ ክፍሎች ጥሩ እንቅስቃሴ ቢኖርም በቀጣይ ክፍሎች ከክፍሎች በመናበብ እና የተለያዩ ስልጠናወችን በማዘጋጀት የተቋሙን ተልዕኮ በይበልጥ ማሳካት አለብን ብለዋል።

በዚሁ ስልጠና ዕለት ተገኝተው የኢንስፔክሽን ስልጠና የሰጡት ብርጋዴል ጀኔራል መዕሾ ኃጎስ እንደገለፁት፣ የሠራዊቱን ወትሮ ዝግጅነት ለማረጋጋጥና ተቋም ውስጥ የመተሳሰብና የመፈቃቀር ባሀልን ለማዳበር ኢንስፔክሽን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለው፣ ብርጋዴል ጀኔራሉ ከተለያዩ ዕዞች፣ ክፍለ ጦሮች እንዲሁም እስታፍ አመራሮች ለተወጣጡ አካላት ስለ ኢንስፔክሽን ምንነትም አብራርተዋል። እንደ ብርጋዴል ጀኔራሉ ገለፃ ኢንስፔክሽን ማለት የቁጥጥር ስራ ሲሆን አላማውም አመረሩ የተቋሙን አሰራር ተከትሎ እንዴት ስራዎችን ማከናወን እንደሚችልና በተቋሙ ውስጥ ያሉ የህዝብ ንብረቶችን በምን አይነት አግባብ መያዝ እንደሚችሉ ለማስገንዘብ የታቀደ ስልጠና ነው።

ከዚህ በመቀጠል ስለ ሴፍቲ ምንነት ስልጠና የሰጡት ብርጋዴል ጀኔራል ደሳለኝ ዳቼ እንደገለፁት ሠራዊቱ ሀገራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እንዲወጣ የኢንስፔክሽን እና ሴፍቲ ስልጠና አስፋላጊ ነው ብለው፣ በተላይም ደግሞ የሴፍቲ ስልጠና ዋና አላማ ሠራዊቱ ግዳጁን በአግባቡ እንዳይፈፅም ሊያደነቅፉ የሚችሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን እንዴት መከላከል እንደ ሚችል ለማስገንዘብ የተሰጠ ስልጠና መሆኑን ገልፀው፣ በቀጣይም ይህ ስልጠና እስከ ታችኛው የሠራዊት አመራር ድረስ እንደሚሰጥ አብራርተዋል።

ሰልጣኞችም ለተከታታይ አምስት ቀናት የተከታተሉት ስልጠና ለቀጣይ ብቁ እንደ ሚያደርጋቸው ተናግረዋል። ከሰልጣኞች መካከል ሌተናል ኮሎኔል መዝገበ ኃይሌ የአየር ኃይል ኢንስፔክተር ዳይሬክተርና ሌተናል ኮሎኔል ኃይለ ማሪያም ተክሉ የሰሜን ዕዝ ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደ ገለፁት ስልጠናው ሠራዊቱ እንዴት ግዳጁን በሚገባ እንደ ሚወጣና አደጋዎችን በምን ዓይነት መልኩ መከላከል እንዳለበት እንዲሁም በተቋሙ ውስጥ ያሉ ንብረቶችን እንዴት መንከባከብ እንዳለባቸው ከስልጠናው በቂ ግንዘቤ እንዳገኙ ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
ኢንተርፕራይዙ ለከፍተኛ የሰራዊት እና ሲቭል አመራሮች ለስድስት ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...