ሞተራይዝድ ሻለቃው የተዘረፉ ከብቶችን አስመለሰ

በሱዳን አብዬ ተልዕኮውን በመወጣት ላይ የሚገኘው የ17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የተዘረፉ 58 የቀንድ ከብቶችን አስመለሰ።

በቀንድ ከብቶቹ የርክክብ ሥነ - ሥርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የዩኒስፋ ኃይል አዛዥ ተወካይ ብርጋዲየር ጄኔራል አሰፋ ገብሩ አንደገለጹት፤ ሻለቃው ከአካባቢው ማህብረሰብ ጋር በመግባባትና በመረዳዳት የተዘረፉ የቀንድ ከብቶችን በማስመለስ ያደረገው ጠንካራ ስራ የሰላም መፍጠር ባህሉን የሚያጎለብት ከመሆኑም ባሻገር ሠራዊቱ ለህዝብ ያለውን አመኔታ ይበልጥ የሚያሳይ ነው።

 

አዛዡ አክለውም፤ ሠላምን ለማስቀጠልም የአካባቢው ማህበረሰብ ከዩኒስፋና ከሞተራይዝድ ሻለቃው ጎን በመሆን ምን ጊዜም ለሠላማቸው እንቅፋት የሆኑት ለይተው ማውጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

 

በተመሳሳይ ዜና በሱዳን አብዬ ዲፍራ የሚገኘው የ17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ተልዕኮውን በአስተማማኝ ለመፈጸም የሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

 

የ17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ኃይሉ ገብረህይወት እንደገለጹት፤ ሻለቃው ግዳጁን ከተረከበ ጀምሮ የዝግጁነት አቅሙን የሚያጎለብቱ ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል።  የዩኒስፋን ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸም ብሎም በአካባቢው ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥ ሠራዊታችን ምንጊዜም የሠላም አምባሳደርነቱን ከመቼውም ጊዜ በላይ እያረጋገጠ ይቀጥላል ብለዋል።

 

የሞተራይዝድ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ሌተናል ኮሎኔል ሀፍቱ ተካ በበኩላቸው፤ ሞተራይዝድ ሻለቃው ግዳጁን ለማከናወን የታጠቃቸውን ወታደራዊ መሳሪያ ዎችና ቁሳቁሶች በእንክብካቤና በአግባቡ ይዞ ለግዳጅ ከማዋል አኳያ ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና የግዳጅ ቀጠና ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
በዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዠ ሜ/ጄ ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብየ ሰሜን ቀጠና የሚገኘውን የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሃይል አሰፋፈርና...
ነሐሴ 26 12 2012 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ነሐሴ 17 12 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ ረፋድ አስመርቋል
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአቅም ግንባታ ግብ ፣ በሁሉም አውዶች መፋለም የሚችል...
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ሴቶች ጉዳይ ከመቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ የምግብ ፍጆታዎችን ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ
በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፤ የመከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር...