የሰው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ሥልጠና ሰጠ

 

የመከላከያ የሰው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ የአመራሩንና የስታፍ  ባለሙያውን አቅም ለማጎልበት የሰጠውን ሥልጠና አጠ ናቀቀ፡፡

ዋና መምሪያው ለሦስት ተከታታይ ቀናት በመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ያካሄደው ሥልጠና ሲጠናቀቅ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ባደረጉት ንግግር፤ ሠልጣኞች አሰራርና ደንብን መሰረት ያደረገ እንዲሁም ተጠያቂነትን እና ኃላፊነትን ያማከለ ስራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ጄኔራል መኮንኑ በዚሁ ንግግራቸው አክ ለውም፤ ሠራዊቱ ለሚሰጠው ማንኛውም ግዳጅ የሰው ሀብቱን ብቃትና ክህሎት በማዘመንና ዝግጁነትን በማሳደግ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ሥልጠናውን የመሩት እና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ የሰው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል አጫሉ ሸለመ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ሥልጠናው የተዘጋጀበት ዋና ዓላማ ከዚህ በፊት ያጋጥሙ የነበሩ የሠራዊቱን የመረጃ  አያያዝና አጠቃቀም እጥረት ለመቅረፍ እና ሠራዊቱ ከቅጥር እስከ ስንብት፤ በጋብቻ፤ በማዕረግና ሌሎች የመሳሰሉት ጉዳዮች ህጉን ተመርኩዞ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል ነው፡፡

በሥልጠናው ላይ የዕዝ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የየክፍሉ የሰው ሀብት ቢሮ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ የሰው ኃይል ስምሪትና ዕድገት መምሪያ፤ የሰው ኃይል የቅጥርና ስንብት መምሪያ፤ የሰው ኃይል መረጃና ማስረጃ ማዕከል እንዲሁም የሰው ሀብት ልማትና ዕቅድ መምሪያ ኃላፊዎች ጥናታዊ ጽሁፎችን አቅርበዋል፡፡

ጥናቶቹን መሠረት አድርገው በተነሱት ሃሳቦች ላይም ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያ ቄዎች ያነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም በሥልጠናው ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ሓምሌ 05 11 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና