ትምህርት ቤቱ ሠላም አስከባሪ ኃይሎችን አስመረቀ

በሠላም ማስከበር ዋና መምሪያ የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ወደ አብዬ የሚሰማሩ የ18ኛ ሞተራይዝድ ሬጅመንት፣ የሲግናል ስታፍ ሻምበል ዩኒት እንዲሁም የአሚሶም 19ኛና 22ኛ ሞተራይዝድ ሬጅመንቶችና የሴክተር 3 እና 4 ስታፍና ሲግናል ዩኒቶችን አስመረቀ።

 

ሰሞኑን ለሁለተኛ ጊዜ በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የእውቅና ምስክር ወረቀት በመስጠት ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ልማት ብ/ጄኔራል ሹማ አብደታ እንደገለፁት፡ ሠራዊታችን ከዘመናዊ ሠራዊት የሚጠበቁ ተግባራትን በማከናወንና ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር እሴቱን ታጥቆ በሀገር ውስጥና በሠላም ማስከበር ግዳጅ በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

ጄኔራል መኮንኑ አክለውም፡ የሠራዊታችን ውጤታማ ተልዕኮ አፈፃፀም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በአፍሪካ ህብረትና ለሰላም ማስከበር በተሰማራባቸው ሀገሮች መንግስታትና ህዝቦች ጭምር ከፍተኛ አድናቆትና ክብር እያገኘ እንደሚገኝ አውስተው፡ የዕለቱ ተመራቂዎችም ስኬታማ ተግባሮችን በማስፋት የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ይበልጥ በሚያረጋግጥ መልኩ ግዳጃቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሠላም ማስከበር ዋና መምሪያ የዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ኃላፊ ብ/ጄኔራል ሀብታሙ ጥላሁን በበኩላቸው፡ የሠራዊታችን ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም አገራችን በተባበሩት መንግስታትና በአፍሪካ ህብረት ያላት ተሰሚነትና ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲሄድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። በአለም አቀፍ ደረጃም በሠላም ማስከበር በቀዳሚነት እንድትገኝ ማስቻሉን ተናግረዋል።

በአለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ግዳጅ የሚሰማሩ አሃዶዎች አለም አቀፍ ግዳጅ ለመፈፀም የሚያስችላቸውን የአካል ብቃት፣ የስነ-ልቦና ትምህርት እንዲሁም የተባበሩት መንግስታትና የአፍሪካ ህብረት አሰራሮችና ደንቦችን ጠንቅቀው በማወቅ ግዳጃቸውን ለማሳካት የሚያስችላቸውን ስልጠና መውሰዳቸውን በሪፖርታቸው ያረጋገጡት ደግሞ የኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ይርዳው ገብረመድህን ናቸው።

 

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
ዋና መምሪያዉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለሰራዊቱ ክፍሎች አስረከበ
የህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ለሰራዊቱ የግዳጅ አፈፃፀም የሚያገለግሉ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በምድር ሃይል ግቢ በመገኘት ለየእዝ አመራሮችና ለመምሪያ ሃላፊዎች ቁልፍ አስረክቧል፡፡