ዕዞቹ ውጤታማ የግዳጅ አፈጻጸም አስመዘገቡ

የምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በበጀት ዓመቱ የተሻለ የግዳጅ አፈጻጸም ማስመዝገቡን የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተና ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም ገለጹ።

ጄኔራል መኮንኑ ይህንን የገለፁት የዕዙን የግዳጅ ቀጣና ለመጎብኘት የተንቀሳቀሰውን ቡድን መርተው ሰራዊቱ ጋር በተገኙበት ውቅት ነው።

እንደ ጄኔራል አብርሃ ንግግር፤ የዕዙ የግዳጅ ቀጣና ውስብስብ ግዳጆች ያጋጥማሉ ተብለው የሚታሰቡ ቢሆንም፤ ትልልቅ የሀገሪቱ የልማት አውታሮችን ደህንነት በመጠበቅ፣ በከባቢው ተከስቶ የነበረውን ሁከት ከህብረተሰቡ ጋር ተባብሮ በማረጋጋት ከህዝቡ ከፍተኛ አክብሮትና ፍቅር ማትረፍ መቻሉን ገልጸው፤ ዕዙ ይህን አኩሪ ተግባሩም አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜ/ጄኔራል ፍስሐ ኪዳኑ በበኩላቸው፤ በበጀት ዓመቱ ዕዙ ተልዕኮውን መነሻ በማድረግ መጠነ ሰፊና ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል።

የዕዙ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጄኔራል ድሪባ መኮንን በበኩላቸው፤ ዕዙ ከኤርትራ የሚላኩ ፀረ-ሠላም ኃይሎችን ተግባር በመግታትና ተከታትሎ በመደምሰስ አኩሪ ሥራ መስራቱን ገልጸዋል ሲል የዕዙ ሪፖርተር ም/መ/አለቃ ልደት አስረስ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና በሌ/ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ የተመራው ልዑካን ቡድን የደቡብ ምሥራቅ ዕዝን የሥራ አፈጻጸም ጉብኝቷል።

ሌ/ጄኔራል አብርሃ በጉብኝቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ሠራዊቱ ህገ-መንግሥቱንና ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከማንኛውም አደጋ በአስተማማኝ የሚጠብቅ፣ ብቃትና ዲስፕሊን ያለው ጠንካራ ዘመናዊ ሠራዊት እንዲሆን ኑሮውና ጤንነቱ የተጠበቀ መሆን አለበት ብለዋል። የዓመቱም የሥራ አፈጻጸም በቀጣይ የተሻለ ሥራ ለመሥራት እንደሚረዳም ገልጸዋል።

በዕለቱም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል የክልሉ መንግሥት የገዛቸው የውሃ ማመላለሻ ቦቴዎች በልዑካን ቡድኑና በዕዙ አመራሮች መጎብኘታቸውን የዕዙ ሪፖርተር ፲ አለቃ አወል መሀመድ ዘግቧል።

በሌላ በኩል የደቡብ ምሥራቅ ዕዝ በተሰማራበት በሌላ በኩል የደቡብ ምሥራቅ ዕዝ በተሰማራበትየግዳጅ ቀጣና ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን ዋና አዛዡ  ሜጄር ጄኔራል ማዓሾ በየነ አመለከቱ።

ጄኔራል መኮንኑ ይህንን የገለጹት ዕዙ ሰሞኑን ባካሄደው የ2009 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ነው።

ዋና አዛዡ እንዳሉት፤ ዕዙ መመሪያና አሰራሮችን መሠረት አድርጎ ባከናወናቸው ተግባራት የአል-ሸባብን ኃይል በማዳከምና በመደምሰስ፣ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት የፀጥታ ኃይል በማጠናከር፣ ዝግጁነቱን አጠናክሯል። ይህ ውጤትም መመሪያና አሰራሮችን በማስረጽ ሠራዊቱ ከአፍሪካ ህብረትና ከፀጥታው ምክር ቤት ላገኘው ከበሬታ ወሳኝ ድርሻ መወጣቱን ዋና አዛዡ መግለጻቸውን የዕዙ ሚዲያ አባል ፲አለቃ አወል መሀመድ ዘግቧል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!