አቶ ለማ መገርሳ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 34ኛውን መደ በኛ ስብሰባ ባካሄደበት ዕለት ክቡር አቶ ለማ መገርሳን የመከላከያ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል።

ምክር ቤቱ ሹመቱን ባጸደቀበት ዕለት እንደ ተገለፀው አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መን ግሥትን በብቃት በመምራታቸው ለበለጠ ኃላፊነት ተሹመዋል። 

የክልሉ መንግሥት ለአቶ ለማ መገርሳ በአዳማ ከተማ የሽኝት ፕሮግራም ባካሄደበት ዕለት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባደረጉት ንግግር፤ አቶ ለማ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በርካታ ለውጦች  ያስመዘገቡ ሲሆን፣ ለከፍተኛ ኃላፊነት መሾ ማቸውንም ገል ፀዋል።

አቶ ለማ መገርሳ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ውስጥ ጉደያ ቢላ በሚባል ወረዳ ተወልደው ያደጉ ሲሆን፣ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትም ህርታቸውንንም በዚያው ቦታ ተከታ ትለዋል።

ከዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በፖለቲካል ሳይንስ እና በዓለም አቀፍ ግንኙንት የባችለር ዲግሪ እና የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ለተወሰኑ ዓመታት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት አቶ ለማ፤  በክልሉ ፀጥታ እና ሠላም በማስፈን እንዲሁም በሌሎች በርካታ ሥራዎች በሚገባ አገልግለዋል።

ለክልሉ እና ለሀገሪቱ ያበረከቱትን  ውጤታማ ሥራ ምክንያት በማድረግም የጅማ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል።

አቶ ለማ መገርሳ በክልሉ በርካታ ሥራዎች እንዲሰሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን፣ በቀ ጣይ በመከላከያ ሚኒስትር የተጀመረውን ሪፎርም በማጠናከርና ፕሮፌሽናል ሠራዊት በመገንባት ጉልህ አመራር እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሆነው ሲያገ ለግሉ የቆዩት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በተቋሙ በርካታ ሥራዎች እየሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒ ስቴር ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ ተሹ መዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ሓምሌ 05 11 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና