የሀሰት ዜና

ሰሞኑን  <<በሃገራችን በሚታየው ስረዓት አልበኝነት ላይ እርምጃ ሊወስድ መሆኑንየ ኢፌዲሪ መከላከያ አስታውቃለሁ›› ተብሎ የተሰራጨው ወሬ ሀሰት መሆኑን ሚኒስቴር መስራያ ቤቱ ያስታውቃል፡፡

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት እንደተkም ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር ለህዝብ የተሟላ ሰላም ምንግዜም በተጠንቀቅ ዘብ የቆመ መሆኑን መላው ህዝባችን የሚያውቀው እውነታ ነው፡፡

ተkሙ ማንኛውንም ተልዕኮ ሲፈፀም ለህገ-መንግስቱ መርህና መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ ሲሆን ማናኛውም ተልዕኮ እንደየግዳጁ ባህሪ መፈፀም የሚችልባቸው ተkማዊ ደንብ መመሪያዎችና አሰራሮች ብሎም የግዳጂ አፈፃፀም መመሪያዎች አሉት፡፡

ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ-ገፅ የተለቀቀው እየተናፈሰ የሚገኘው ሃሰተኛ መረጃየ ተkሙን ሁለተናዊ ያሰራርና የግዳጅ አፈፃፀም መርህ የጣሰ መሆኑንና በአድራሻነት የተጠቀሱት የስልክ የፖስታና የድረ-ገፅ አድራሻዎችም ከተግባራቸው ጋር የማይገናኝ መሆኑን መላው ህዝብ እነዲያውቀውና በዚህ እንዳይታለል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታውቃል፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!