የካምፕ ግንባታ ሥራ ተከናወነ

 

በምዕራብ ዕዝ የ42ኛ ክፍለ ጦር መሃንዲስ ሙያተኞች የሠራዊቱን የመኖሪያ ችግር ለመቅረፍ የግንባታ ሥራ አከናወኑ።

የክፍለ ጦሩ መሃንዲስ ቡድን መሪ ኮሎኔል መሃመድ ጀማል እንደገለጹት፤ በግንባታው እየተሰሩ ያሉት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ እና አሁን ያለውን የካምፕ ችግር የሚቀርፉ ናቸው ብለዋል።

 ከፍተኛ መኮንኑ  አያይዘውም ግንባታው እየተካሄደ ያለው ከመከላከያ በተመደበ በጀት በሠራዊቱ ሙያተኞች እና የጉልበት ድጋፍ መሆኑ ወጪ ቆጣቢ እና አላስፈላጊ የገንዘብ ብክነትን ይከላከላል ሲሉ ገልፀዋል።

የክፍለ ጦሩ ኮንስትራክሽን መሃንዲስ ሻምበል ተወካይ የሆኑት ሻለቃ ጥዑምፈል ከበደ በበኩላቸው፤ እየተገነቡ ያሉት ቤቶች ዲዛይን ወጥቶላቸው በዘመናዊ መልክ የተሰሩ ሲሆን የሻምበል እና የመቶ አመራሮችን እንዲሁም አባላትን ከነሙሉ ትጥቃቸው የሚይዙ ናቸው ብለዋል።

የግንባታ ሥራውን ካከናወኑት የኮንስትራክሽን ሙያተኞች መካከል ያነጋገርናቸው መ/አለቃ እንድሪስ አሊ እና መ/አለቃ አየለ ፀጋዬ በሰጡት ማብራሪያ በሙያው ሥልጠና በመከላከያ እንደተሰጣቸው እና በተለያዩ የግንባታ ሥራዎች በመሳተፋቸው የሠራዊቱን መጠለያ ችግር ከመፍታት ባሻገር የሙያ ክህሎታቸውን በየጊዜው እየዳበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሠራዊቱ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ተባለ

በአወል መሃመድ (% አለቃ)

የዕዝ ሪፖርተር

 

 

በባይደዋ የተሰማራው የሴክተር 3 ሠላም አስከባሪ ሻለቃ የአካባቢውን ሠላም አስተማማኝ ከማድረግ ባሻገር በአካባቢው የተለያዩ መሠረተ ልማቶች በመዘርጋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያዳረጉ ነው።

የሴክተር 3 ውሃ ቁፋሮ ዩኒት አዛዥ ሌተና ኮሎኔል ቴዎድሮስ ሃዱሽ እንደተናገሩት፤ በተሰማሩበት የግዳጅ ቀጣና የውሃ አቅርቦትን ለማሟላት አራት የውሃ ጉድጓዶችን መቆፈራቸውን ጠቅሰው፤የአካባቢውን ህብረተሰብ የውሃ ተደራሽነት በማስፋት ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። በዚህም የሀገራችንን መልካም ገጽታ ለመገንባት የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

ከውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሙያተኞች መካከል ሻለቃ ይብሳ ጉሱና %አለቃ ተስፋዬ ንጉሴ በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት፤ ሙያተኛው የአካባቢው ተለዋዋጭ የአየር ፀባይ በመቋቋም ተልዕኮውን በጽናት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ሓምሌ 05 11 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና