የአካባቢ ጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

 

በማዕከላዊ ዕዝ በ331ኛ ማርታ ሬጅመንት የሠራዊት አባላት በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩትን የጤና ችግሮች ለመከላከል በርካታ ሥራዎችን እያከናወኑ መሆኑ ተገለፀ።

የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት ሌተና ኮሎኔልብርሃኔ ተስፋዬ እንደተናገሩት ወቅቱ ክረምት እንደመሆኑ የወባ ትንኝ የሚስፋፋበት ስለሆነ ሠራዊታችን በአካባቢው የሚገኙ ቆሻሻዎችን እንዲያስወግዱ እና እንዲያፀዱ በማድረግ የአካባቢውን እና የራሱን ንጽህና መጠበቅ ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

የሬጅመንቱ ጤና ኃላፊ ሻምበል መሰለ አሰፋ በበኩላቸው፤ የዕርጥብ እና የደረቅ ቆሻሻዎችን የማስወገጃ ጉድጓዶችን በመቆፈር የመቅበር ሥራ የተሰራ ሲሆን በርካታ የውሃ ማቆሪያ ጉድጓዶችን በመድፈን የወባ ትንኝ እንዳይስፋፋ በማድረግ ከክረምት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የጤና እክሎችን አስቀድሞ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሠራዊቱ ከዚህ በበለጠ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

በጽዳት ዘመቻው ተሳታፊ ከነበሩት አባላት መካከል የተወሰኑት በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት ወቅቱ ክረምት እንደመሆኑ ሁላችንም የሚፈጠሩ የጤና እክሎችን ለመከላከል አስቀድመን ሥራ በመሥራት እና ጤናችንን በመጠበቅ ህዝብ እና መንግሥት የጣሉብንን አደራ መወጣት ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።

በልዩ ልዩ ክፍሎች የደም     ልገሳ ተደረገ

የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሃገሪቱን ልማት በዘላቂነት እንዲቀጥል በገንዘብ ከመደገፍ ባሻገር የደም ልገሳ አደረጉ።

በዚህም መሰረት በማዕከላዊ ዕዝ የ222ኛ ሬጅመንት የሠራዊት አባላት “ደም በመለገስ የወገንን ህይወት እንታደግ” በሚል መሪ ቃል በበጎ ፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ደም ለግሰዋል።

የአክሱም ደም ባንክ  ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን የማነ እንደተናገሩት፣ በየሆስፒታሉ ደም ለሚያስፈልገቸው ወገኖች የሚሆን ሠራዊቱ በራስ ተነሳሽነት እያደረገ ያለው ደም የመለገስ ተግባር አሁን ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጊዚያትም አጋርነቱን እየገለፀ የመጣ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሠራዊቱ በሚለግሰው  ደም የብዙ ሰው ህይወት ለማትረፍና በተለይ እናቶች በወሊድ ምክንያት ሲያጋጥማቸው የነበረ የሞት አደጋ ለመቀነስ እገዛ አድርጓል ብለዋል።

ደም ሲለግሱ ያገኘናቸው የሠራዊት አባላት እንደገለፁት፣ የወገንን ህይወት ለማዳን ደም በመለገሳቸው ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመው በደም እጦትሊሞቱ የሚችሉ ወገኞች ህይወታቸውን ለመታደግ በቀጣይነት  የደም ልገሳ ፕሮግራም እንደሚያደርጉ የሬጅመንቱ ሪፖርተር ም/፲/አለቃ ሸዊተይ በሪሁ ዘግቧል።

በተያዘ ዜና በማዕከላዊ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሬጅመንት የሠራዊቱ አባላት አመራሮች በበጎ ፍቃደኝነት የደም ልገሳ አደረጉ።

በዕለቱ ደም ከለገሱት የሠራዊቱ አባላትና አመራሮ መካከል ያነጋገርናቸው አባላት በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት፣ በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችና በተለያዩ ችግር ደም አጥተው የሚሞተው የህብረተሰብ ክፍሎችን ህይወት እኛ በምንሰጠው ትንሽ ደም መታደግ ማለት እጅግ በጣም የሚያስደስት ተግባር ነው ማለታቸውን የዘገበው የሬጅመንቱ ሪፖርተር ፲አለቃ ባበው ዘውዴ ነው።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
የክቡር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የህይወት ታሪክ
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከአባታቸው ከ፲አለቃ መኮንን ይመር አና ከእናታቸው  ከወ/ሮ ሂይወት ይህደጎ ተላ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ምጽብላ...
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
ኮሌጁ ሶስተኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ
የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ሦስተኛውን ሀገርአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ።
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
ፋውንዴሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ሊያስረክብ ነው
የመከላከያ  ፋውንዴሽን  በመጀመሪያ ዙር ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ ለሠራዊቱ በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ...
ሰኔ 14 10 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና
ሓምሌ 05 11 2011 መከላከያ ሬዲዮ ዜና