የቤት ግንባታው ተጠናቀቀ

 

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የገነባነውን የቤት ግንባታ አጠናቆ ለሠራዊቱ ለማደል ዝግጁ መሆኑን ተገለጸ።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሜጄር ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል እንደገለጹት፤ የሠራዊቱን ፍላጎት ለማሳካት በፍጥነትና በጥራት ዘመናዊ አፓርታማዎች እንዲሰሩ የሠራዊቱ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፤ ግንባታው በስኬት እንዲጠናቀቅ የገቢ ምንጫቸው ሠራዊቱ ስለሆነ በቀጣይም የመከላከያ የሠራዊት አባላት በየጊዜው ከወር ደመወዛቸው በመቆጠብ የግንባታ ሥራው በዘላቂነት እንዲቀጥልና እራሱን ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።

የመከላከያ ፋውንዴሽን የቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ታደሰ ጌታቸው በበኩላቸው፤ ፋውንዴሽኑ ከመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር  በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ አፓርታማዎች በአዳዲስ ቴክኖሎጂ መሠራታቸውን ገልጸው፤ ማንኛውም የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሚጠበቅባቸውን የቅድሚያ ክፍያ 20 በመቶ  ካጠናቀቁ  በደንብና መመሪያ መሠረት ግልጽነትና ፍት ሃዊነት ባለው መልኩ እንደሚታደልና በቀጣይም አዳዲስ ግንባታዎች የተለያዩ ከተሞች ላይ እንደሚጀመሩ ተናግረዋል።

በሠላም ማስከበር ተልዕኮ     የሚሰማሩ ሻለቆች ተመረቁ

በአሰፋ በለው (ሻምበል)

የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሠልጠኛ ት/ቤት ሪፖርተር

 

በተባበሩት መንግሥታት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ የሚሰማሩ ሞተራይዝድ ሻለቆች ተመረቁ።

በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በተከናወነው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት የመመሪያ ንግግር ያደረጉት በሠላም ማስከበር ዋና መምሪያ የሎጀስቲክ ዝግጅትና ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ከበደ ረጋሳ በአህጉራችን አፍሪካ በሚከሰቱ ግጭቶች ንጹሃን ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመከላከልና የጎረቤት ሀገራትን ሠላም ለማረጋገጥ የተሰጣችሁን ተልዕኮ በህዝባዊ ወገንተኝነትና ቁርጠኝነት መወጣት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

በመከላከያ ሠላም ማስከበር ዋና መምሪያ የኮንቲጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ሚልኬሳ ረጋሣ በበኩላቸው በቅድመ ስምሪት ሥልጠናው ተፈላጊው አቅም መፈጠሩን ተናግረዋል።

ሻለቆቹ በተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ  ሱዳን አብዬና በአሚሶም የሶማሊያ ተልዕኮ የሚሰማሩ ናቸው።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!