ትምህርት ቤቱ ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀሙን በስኬት አጠናቀቀ

 

በአዋሽ አርባ የሚገኘው የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት የ2010 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀሙን በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

በፕሮግራሙ ላይ የትምህርት ቤቱ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሙዘይ መኮንንን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። ብ/ጄኔራል ሙዘይ መኮንን በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክትም በ2010 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም በዓመቱ መግቢያ ላይ ተይዞ የነበረው ዕቅድ በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን ገልፀዋል።

ጄኔራል መኮንኑ አያይዘውም የፕሮግራሙ ዋነኛ ዓላማ ለዕቅዱ ስኬት የጎላ ሚና ላበረከቱት ዲፓርትመንቶችና ግለሰቦች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ለመስጠት፣ እንዲሁም በሠራዊት አባልነት የአገልግሎት ዘመን 10 ዓመትና ከዛ በላይ ለሆናቸው የሠራዊት አባላት የክብር ሜዳሊያና ሪባን ለመሸለም እንደሆነ ብርጋዲየር ጄኔራል ሙዘይ መኮንን ገልፀዋል።

በዕለቱም የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት የተካሄደ ሲሆን፤ ሽልማትና እውቅና መሰጠቱም በቀጣይ የሥራ መነሳሳትን እንደሚፈጥርላቸው ሽልማቱ የተበረከተላቸው የሠራዊት አባላት በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት ገልፀዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!