በፌዴራል የፀጥታ ምክር ቤት የተዘጋጀ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

 

   

 

በፌዴራል የፀጥታ ምክር ቤት የተዘጋጀ እቅድን መሰረት በማድረግ የሀገሪቱን  ወቅታዊ ሁኔታ የሚገመግምና የፀጥታ ስራው የሚመራበትን አቅጣጫ ያመላከተ ውይይት በመከላከያ አዲስ አበባ በመኮንኖች ክበብ ተካሄደ፡፡

የውይይት መድረኩ በሀገሪቱ ያለውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ሁሉም ስራዎች በህግ ማዕቀፍ ተካተው እንዲከናወኑና የህግ የበላይነት ማስከበር ላይ ትኩረት ሰጥቷል፡፡

የህብረተሰቡን ሠላም በዘላቂነት ለማስጠበቅና በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታየውን የፀጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር ሁሉም በየደረጃው የሚገኝ የፀጥታ መዋቅር አካላት በትኩረት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን  አሳስበዋል፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን በበኩላቸው የኢፌዴሪ መከላከያ  ሠራዊት የተቀበለውን ህገ - መንግስታዊ ተልዕኮ በላቀ ብቃት በመፈፀም በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የታየውን የሠላም እጦት ለማስቀረት ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተባብሮ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የሁሉም ክልል መስተዳድሮች፣ የፌዴራልና የክልል ፀጥታ አመራሮች በውይይቱ የተካፈሉ ሲሆን  የህግ የበላይነት እንዲከበር በትኩረት ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን በቅንጅት ለማስወገድና የሀገሪቱን ሠላማዊ ጉዞ ለማረጋገጥ ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፤ በመጨረሻም በፌዴራል የፀጥታ ምክር ቤት በተዘጋጀው የፀጥታ ሥራ ማስፈፀሚያ እቅዱ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቶ ሁሉም አካል ተልዕኮውን በመቀበል መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!