የሠራዊት አባላቱ የህዳሴ ግድብን ጎበኙ

 

በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ኢንዶክትርኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በብርጋዴር ጄኔራል ኑር ሙዘይን የተመራ የሠራዊት አባላት ያቀፈ ቡድን የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጎበኙ።

ስለ ጉብኝቱ አጠቃላይ አላማ በማስመልከት ጄኔራል መኮንኑ በሰጡት ገለፃ፣ ሠራዊቱ እንደ ተቋም የተሰጠውን ህገ- መንግስታዊ ኃላፊነት ከመወጣት ጎን ለጎን በሃገሪቱ ልማት  በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ በመሳተፍ የበኩሉን እያበረከተ እንደሆነ ተናግረዋል።

ጉብኝቱ የዕዙን አባላት በየደረጃው ያሳተፈ ከመሰረታዊ ወታደር እስከ ጄኔራል መኮንን ያካተተ ነው።የዕዙ አባላት ለታላቁ የህዳሴ ግድብ እንደሌሎች ዕዞች ሁሉ ለተከታታይ 7 ዓመት ከደሞዙ ቦንድ በመቁረጥ እና የገንዘብ ስጦታ በማበርከት ላይ ይገኛል፤ ይህን ታላቅ ሃገራዊ ፕሮጀክት በቦታው ተገኝቶ መጎብኘቱ በጎብኚው ላይ ከፍተኛ ተነሳሽነት የሚፈጥር እና በግድቡ ስራ ላይ የሚሳተፉ ሰራተኞችን ከፍተኛ ብርታት  የሚሰጥ መሆኑን ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን ገልፀዋል።

“ወደ ታለቁ ህዳሴ ግድብ እንኳን ደህና መጣችሁ” በማለት መልካም ምኞታቸውን በማስቀደም ግድቡን ያስጎበኙት ሲነር ላብራቶሪ ቴክኒሽያን የሆኑት አቶ ሽፈራው ዳምጤ ሲሆኑ፣ ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አክብሮትና አድንቆት ገልጸው፣ ሠራዊቱ ለግድቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አድንቀዋል። ፕሮጀክቱ ከተጀመረበት እለት ጀምሮ የመከላከያ ሠራዊት ቀን እና ሌሊት በመጠበቅ እንዲሁም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ቦንድ በመግዛትና ከዛም አልፎ የገንዘብ ስጦታ በመስጠት በግድቡ ስራ ላይ በቀጥታ በመሳተፍ ወርቃማ አሻራውን በማኖር የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!