በልዩ ልዩ የሠራዊቱ ክፍሎች ሥልጠና ተሰጠ

 

በሠራዊታችን ልዩ ልዩ ክፍሎች የአቅም ማጎልበቻ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በዚህም መሰረት በ23ኛ ክፍለ ጦር የአቅም ማጎልበቻ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። በስልጠናው ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል አድማሱ አለሙ እንደተናገሩት፣ የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደት ስኬታማ እና ውጤታማ እንዲሆን በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የሠራዊቱ አመራሮች በሚያከናውኑት ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ጠንክረው በመስራት አርአያ መሆን ይገባቸዋል።

የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖች እና ከፍተኛ የበታች ሹሞች ሲሆን በስልጠናው ላይ የተለያዩ  ይዘት ያላቸው መመሪያዎች እና ደንቦች በጥልቀት መዳሰሳቸውን የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፲ አለቃ ፍሬዘር በሪሁ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና በባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ 30ኛ ክፍለ ጦር ከመጋቢ ፶ አለቃ እስከ ሻለቃ ላሉ አመራሮች የሠራዊት ግንባታ ምንነትን በተመለከተ ለተከታታይ አስር ቀናት ስልጠና ተሰጠ።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጀማል መሃመድ፣ “በተማራችሁበት ትምህርት ላይ ያገኛችሁትን ክህሎት ወደ  ተግባር በመለወጥ ሃገርና ተቋም በሚፈልገው ደረጃ የአሀዱን ግንባታ ማስቀጠል አለባችሁ” ብለዋል።

በስልጠናው ተሳትፈው ከነበሩት መካከል ሻምበል  ጨምር አጋ እና ሻምበል ሃይሉ በየነ በሰጡት  ተመሳሳይ አስተያየት ትምህርቱ ለአመራሮች ከዘልማዳዊ አሰራር እንዲወጡ እና በመመሪያ እና ደንብ አሃድን እንዲመሩ ያስቻለ ስልጠና ነው ማለታቸውን የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፶ አለቃ ደግነት ተስፋዬ ያደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

በሌላ በኩል በሰሜን ዕዝ 16ኛ ክፍለ ጦር ለአሃድ ግንባታ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ ብሎ ያሰለጠናቸውን የወታደራዊ ፖሊስ አባላት አስመረቀ። በምረቃስነ- ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የ16ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕራሽናል ኮሎኔል ሓጎስ ዘማርያም፣ በቀጣይ የሚሰጣችሁን ማንኛውንም ተልዕኮ ደንብና አሰራርን መሰረት በማድረግ የወታደራዊ ፖሊስ አርአያ መሆን ይገባችኋል ማለታቸውን የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር ፲ አለቃ መሃመድ አህመድ ያደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

በተመሳሳይ ዜና ከባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ ክፍለ ጦሮች ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት በኦክስፎርድ ቴክኖሎጂ ቢዝነስ ኮሌጅ በኮምፒውተር ትምህርት ዘርፍ ለሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ።

በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ዕዝ አጠቃላይ  ትምህርት ቡድን መሪ ተወካይ ኃላፊ ሌተና ኮሎኔል በላይ ግርማይ ስልጠናው ለዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ የጎላ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

የኦክስፎርድ ቴክኖሎጂ ቢዝነስ ኮሌጅ ዲን መምህር ሙስጠፋ ኢብራሂም በበኩላቸው የሰልጣኞችን አቅም ለማሳደግ በሁለት ፈረቃ ትምህርቱን በመስጠት ሰልጣኞቹ በቂ አቅም እንድይዙ መደረጉን ገልፀዋል።

በስልጠናው በትምህርታቸው ብልጫ ላመጡ ሰልጣኞች የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ ሽልማት እንደተበረከተላቸውም የማዕከላዊ ዕዝ ሪፖርተር ሻምበል ሙሉጌታ አለባቸው ዘግቧል።

በማዕከላዊ ዕዝ በ331ኛ ማርታ ሬጅመንት  የሠራዊት አባላት የቡድን መሣሪያ ቴክኒክ ሥልጠና ተሰጠ።

በሥልጠናው ወቅት የተገኙት የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት ልማት ኮሎኔል ብርሃነ ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ ካሁን ቀደም በሠራዊታችን የሚገኙ መሣሪያዎች ቴክኒክ ችሎታን የሚያሳድግ እና ተልዕኮን ለማሳካት በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ የሚያጋጥሙ ሞራላዊ እና አካላዊ ፈተናዎችን ለመቋቋም የሚያስችል ሥልጠና  ነው ብለዋል።

የሬጅመንቱ ሥልጠና ተወካይ ሻምበል ባሻ ጓድ ሰንደቄ በበኩሉ፤ የተጀመረው የቡድን መሣሪያ ቴክኒክ ሥልጠና አዲስ ወደ ሠራዊቱ ለተቀላቀሉ የሠራዊት አባላት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው መግለፃቸውን የሬጅመንቱ ሪፖርተር !አለቃ ታምሩ በኃይሉ ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና የምዕራብ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ከክፍለ ጦር እና ስታፍ ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት በሹፍርና ሙያ ለዘጠኝ ተከታታይ ወራት አሰልጥኖ አስመረቀ።

የምዕራብ ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ ኮሎኔል በላቸው ገዳ በምረቃ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፤ የኢፌዴሪ መከላከያ ተቋም የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታን እና የግዳጅ አፈፃፀም ክህሎትን ለማሳደግ በየዘርፉ በማሠልጠን ብቃትን በማዳበር ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችል፤ ሳይንሳዊ ዕውቀትን በመላበስ የሠራዊቱን ግዳጅ አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ነው ብለዋል።

በሥልጠና ቆይታቸው ብልጫ  ላስመዘገቡ ሠልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና የተሽከርካሪ ጥገና ሙያተኞች የቦንድ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት እንደተበረከተላቸው የማሠልጠኛ ማዕከሉ ሪፖርተር %አለቃ ሀብታሙ ገብረፃዲቅ ዘግቧል።

በተመሳሳይ ዜና በባሩድ ማዕከላዊ ዕዝ በ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት ለተከታታይ 30 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የመገናኛ ሥልጠና ተጠናቀቀ።

የሬጅመንቱ ምክትል አዛዥ ለአስተዳደር ሌተና ኮሎኔል ብርሃነ ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ “የግንኙነት ሥራ በባህሪው መልዕክትን ሳይዛባ ለማስተላለፍ ወሳኝ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ያገኛችሁትን ዕውቀት ተጠቅማችሁ በሙያው የተሻለ ውጤት ያለው ሥራ መሥራት ይኖርባችኋል” ብለዋል።

በሥልጠናው ላይ ተሳታፊ የነበሩት አባላት በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት “ያገኘነውን ዕውቀት ተጠቅመን የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ ነን” ማለታቸውን የሬጅመንቱ ሪፖርተር !አለቃ ታምሩ በኃይሉ ዘግቧል።

በሌላ በኩል በሰሜን ዕዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቡድን ከክፍለ ጦሩ ለተውጣጡ የመገናኛ ሙያተኞች ተጨማሪ ሥልጠና ሰጥቶ አስመረቀ።

በዕለቱ የተገኙት የክፍለ ጦሩ የመገናኛ እና ኢፎርሜሽን ቡድን መሪ ሌተና ኮሎኔል ጡዑማይ ገብረስላሴ እንደተናገሩት፤ አሁን የተሰጣቸው ተጨማሪ ሥልጠና ሥራቸውን በሚገባ እንዲወጡ በግዳጅ አፈፃፀማቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል ብለዋል።

በሥልጠናው ወቅት ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ሠልጣኞችም የምስክር ወረቀት እና የማበረታቻ ሽልማት እንደተበረከተላቸው የክፍለ ጦሩ ሪፖርተር %አለቃ ፍቃዱ ጆቴ ዘግቧል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!