ጥምር ኮሚቴው ውይይት አካሄደ

 

የምዕራብ ዕዝ 12ኛ መተማ ክፍለ ጦር አመራሮች  እና የሱዳን 4ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አመራሮች ጥምር ኮሚቴ በቤንሻጉል አሶሳ ከተማ በአካባቢው ፀጥታ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

በጋራ የውይይት መድረክ ላይ በመገኘት ስለ ፀጥታው ጉዳይና አጠቃላይ ስላለው ግንኙነት ንግግር ያደረጉት የቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻዲሌ ሃሰን ናቸው።

ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸውም የኢትዮ- ሱዳን የወንድማማችነት ጉርብትና የቆየና የረዥም ታሪክ ባለቤት ሲሆን ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

የሁለቱም ሃገራት የሠራዊት አባላት በድንበር አካባቢ ጠንካራ የሆነ ስራ በመስራት የቀጣናውን  ሠላም በመጠበቅ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ሃገራትን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባም የክልሉ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።

በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት የ12ኛ መተማ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ብርሃኑ ጥላሁን በበኩላቸው፣ ጥምር ኮሚቴው መልካም የሚባል ተልዕኮን በመወጣት ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው፣ከወታደራዊ ተልዕኮ ጎን ለጎንም የማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር፣ የባህል ልውውጥ እንዲሁም የስፖርት ፌስቲቫል በማካሄድ ወዳጅነታችን ለማጠናከር እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሱዳን ጥምር ኮሚቴን የመሩት  ሜጀር ጄኔራል  አህመድ አብድረሂም በበከኩላቸው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ወደ ቤታቸው የሚሄዱ ያህል እንደተሰማቸውና በቀጣናው ያለው የህገ- ወጥ የመሳሪያና የሰዎች ዝውውር  በጋራ ለመከላከል ከወትሮው በተለየ መልኩ በጠንካራ ሁኔታና ቁጥጥር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!