የሠራዊቱ የፀጥታ ሥራ የጎላ እንደነበር ተነገረ

 

በአሶሳ ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን ፀጥታና ብጥብጥ በማረጋጋት ሂደት እንዲሁም የሰዎች ሂወትና ንብረት እንዳይጠፋ በማድረግ የሠራዊቱ ሚና የጎላ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ይህንን የተናገሩት ሰሞኑን በአሶሳ ከተማ እና በአንዳንድ የክልሉ ከተማዎች ተፈጥሮ የነበረው ሁከትና ብጥብጥ በማውገዝና በከተማዋ ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ባካሄዱት የሰላም ኮንፍረንስ ነው።

ነዋሪዎቹ  ብጥብጡ ክክልሉ የፀጥታ ኃይል በላይ መሆኑ ታውቆ የመከላከያ ሠራዊት ቶሎ ገብቶ ማረጋጋት ባይችል ኖሮ ከዚህ የከፋ ችግርና ጥፋት ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል። ሠራዊቱም የህዝብ ልጅ መሆኑን ያስመሰከረ ስራ እንደሰራ ጠቁመዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የ12ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ኮሎኔል ምሩፅ ወልደ ሚካኤል እንዳሉት ሠራዊቱ ምን ጊዜም ህገ- መንግስቱንና ህገ- መንገስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ የቆመ ሠራዊት እንደመሆኑ  መጠን

የሰራው ተግባርም ይህንን ያስመሰክርለታል እንዲሁም ከግዳጅ ጎን ለጎን ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ወደ ህክምና በማድረስና የህክምና አገልግሎት በመስጠት አስተዋፅኦ ከፍ ያለ እነደነበር ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!