242ኛ ሬጅመንት በሚገኙበት የግዳጅ ቀጣና ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ህገ- ወጥ መሣሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ።
የሬጅመንቱ ተዋጊ መሃንዲስ አባላት ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሠረት የሰሌዳ ቁጥሩ 3-80259 AR አይሱዚ መኪና በቻንሲው ሥር ተበይዶ በተዘጋጀው በሁለት ሳጥን ደብቆ ሊያሳልፍ ሲል 298 የቱርክ ሽጉጥ በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል።
የሬጅመንቱ ዘመቻ ኃላፊ እንደገለጹት፤ ሠራዊቱ ጥቆማ ከደረሰው ጀምሮ ያለ ዕረፍት ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ ባደረገው ብርቱ ክትትልም በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል።
ዜና በመውጫው ምትኩ (ም/መ/አለቃ) Aug 07, 2018 የመረጃ ምንጭ: ወጋገን ጋዜጣ 553 ጊዜ ተነበዋል
ጥቅምት 04 03 2012 መከላከያ ሬዲዮ ዜና |