የሠራዊቱ አመራሮች ተመረቁ

 

በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በሁለተኛ ዲግሪ ተመረቁ።

ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ ለመማር ዕድሉ የተመቻቸላቸው የመከላከያ ሠራዊት አባላት በመልካም አስተዳደር እና የአመራር ጥበብ ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

በዕለቱ ከተመረቁ የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ እንደተናገሩት፤ ትምህርት የአንድ ሀገር ሳይንሳዊ፣ ኢኮኖያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች ለዕድገት መሠረት የሆኑትን ቁልፍ መሳሪያዎችን የሚያጎናጽፍ መሆኑን በመጠቆም ምሩቃን የሠራዊት አባላት የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር በመለወጥ ተቋሙን በሚገባ ማገልገል ይገባቸዋል ብለዋል።

በዕለቱ ተመራቂ የነበሩት የደቡብ ምሥራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት ልማት ጄኔራል ሹማ አብደታ እንዲሁም የመከላከያ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ በሰጡት ተመሳሳይ አስተያየት መማር ለሀገር ወዳድ ዜጎች ትልቅ ኃላፊነት የሚያላብስ እና ቀጥተኛ የልማት ተሳታፊነታቸውን የሚያረጋግጥ እንደመሆኑ መጠን ባገኙት የአመራር ትምህርት ዕውቀት በሚገባ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በጀኔራሎቹ ሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በጀኔራሎቹ ሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
ኢትዮጵያውያን ሁሉ በተፈጥሮ ወታደሮች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ደግሞ የተፈጥሮ ወታደርነትን ከዘመናዊ ስልጠናና ከዲስፕሊን ጋር ያዋሀዱ ምርጦች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ይህ ነው...
ታህሳስ 26 04 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በሰው ኃብት ልማት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ደረጃ ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለሰው ኃብት ልማት ሙያተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ከመከላከያ ሰው ሀብት ዋና መምሪያ...
ጥር 03 05 2012 መከላከያ ቴሌቪዥን ዜና
Video poster
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የሴቶች ጉዳይ በጦር ሃይሎች ከምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ፡፡