የግጭት አፈታትና ቁጥጥር ሥልጠና ተጠናቀቀ

 

በጃፓን መንግሥት ድጋፍ እና በሠላም ማሰከበር ማሥልጠኛ ማዕከል ትብብር ሲሲጥ የነበረው የግጭት መቆጣጠር ሥልጠና ተጠናቀቀ።

በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር የሆኑት ሲንጃ ሳናድ እንዳሉት፤ የጃፓን መንግሥት ኢትዮጵያ ለምታደርገው የቀጣናው የሠላም አስተዋጽኦ የጃፓን መንግሥት ድጋፍ እንደማይለያትና በቅረቡም ከኤርትራ መንግሥት ጋር ያደረጉት የሠላም መፍትሄን መንግሥታቸው እንደሚያደንቅ ገልጸዋል።

አምባሳደሩ አክለውም መንግሥታቸው ኢትዮጵያ በሠላም ማስከበር ሆነ እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ሠላም ለመመለስ ለምታደርገው አስተዋጽኦ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በዚሁ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሠላም ማስከበር ማሠልጠኛ ት/ቤት አዛዥ የሆኑት ብርጋዲየር ጄኔራል ሀብታሙ ጥላሁን ባደረጉት ንግግር፤ “ በሥልጠና ላይ ከአስር የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የሠራዊት አባላት ተሳታፊ እንደነበሩ ገልጸዋል።”

ጄኔራል መኮንኑ አያይዘውም የዚህ ሥልጠና ዋና ዓላማ የሆነው የልዩ ልዩ ሀገራት የግጭት ቁጥጥርና አፈታት ዘዴን ልምድ ለመለዋወጥም ሆነ  ሀገራት ለሚያሰማሩት የሠላም አስከባሪ ሠራዊት አባላት ትልቅ ትምህርት የሚገኝበት እንደሆነ ተናግረዋል። በመጨረሻም ድጋፍ ላደረገው የጃፓን መንግስት ምስጋናቸውን በማቅረብ ለሠልጣኞች ደግሞ መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!