ለሴት የሠራዊት አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ

 

 

ከምዕራብ ዕዝ ልዩ ልዩ ክፍሎች ለተውጣጡ ሴት የሠራዊት አባላት በዕዙ ማሠልጠኛ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጣቸው።

ለሴት አባላቱ በተሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ የነበሩትና በአሁኑ ሰዓትም የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ፍሰሃ ኪዳኑ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ላይ፤  ሴት የሠራዊት አባላት በመልካም ሥነ- ምግባር ታንፀው በታላቅ ሙያዊ ፍቅር የመሪነት ሚናችውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ጄኔራል መኮንኑም አክለውም እንደተናገሩት፤ ለአንድ ወር በተዘጋጀው በዚህ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ላይ ሴቶችን የተመለከቱ ህጎች ማዕቀፎች ጨምሮ በተለያዩ የተቋሙ መመሪያና ደንቦች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች ተሰጥተዋል። ሥልጠናው ነባር ሴት የሠራዊት አባላትን እና በቅርብ ወደ ሠራዊታችን ከተቀላቀሉት ጋር ያገናኘ በመሆኑ ትልቅ ተሞከሮ መለዋወጫ መድረክም እንደነበር ገልፀዋል።

የዕዙ ሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ሌተና ኮሎኔል ብርጭቆ ገብረስላሴ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ሠልጣኞች በቆይታቸው ሴቶችን በተመለከተ በልዩ ልዩ  ህጎችና ተቋማዊ ደንቦች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲይዙ ተደርጓል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!