ድጋፍ ሰጪና ሄሊኮፕተር ዩኒቶች የሜዳሊያ በአላቸውን አከበሩ

 

በአብዬ ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የሚገኙት የድጋፍ ሰጪ እና የሄሊኮፕተር ዩኒት የሠላም አስከባሪ ኃይል አባላት የሜዳሊያ በአላቸውን አከበሩ።

በድጋፍ ሰጪ ዩኒት በተካሄደው የሜዳሊያ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት በግዳጅ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አባላት የተዘጋጀላቸውን ሽልማትና ሜዳሊያ ያጠለቁት የዩኔስፋ የበላይ ጠባቂ ተወካይና የኃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ በዕለቱ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት በተሰማራበት ግዳጅና ቦታ ሁሉ ሀገሩን ስለሚያስብ ተደራጅቶ ስለሚሰራና ግዳጁንም በጀግንነት ስለሚወጣ ውጤታማ መሆን አስችሎታል። ዩኒቱም የዚህ ሠራዊት አካል በመሆኑ ስኬታማ ለመሆን ችሏል ብለዋል።

የድጋፍ ሰጪ ዩኒቱ አዛዥ ሻለቃ ዘመዱ ደሱ በበኩላቸው፤ ዩኒቱ ለዋናው ማዘዣ ተልዕኮዎች ስኬት የራሱን ድርሻ እየተወጣ ያለ መሆኑን ጠቁመው፤ በግዳጅ አፈፃፀም ሂደቱም ውጤታማ ተግባር ማከናወኑን ገልፀዋል ሲል የዩኒቱ ሪፖርተር መ/አለቃ ክንፈ አስገዶም ከስፍራው ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

በተመሳሳይ ዜናም በአብዬ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የሚገኘው የ6ኛው ዙር ሄሊኮፕተር ዩኒት አባላት የሜዳሊያ በአላቸውን አከበሩ።

በበዓሉ ላይ በመገኘት በሥራ አፈፃፀማቸው ውጤታማ ለሆኑ አባላት ሽልማት በመስጠትና ሜዳሊያ በማልበስ የሥራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የዩኔስፋ ኃይል አዛዥና የበላይ ጠበቂ ተወካይ ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ እንደተናገሩት፤ የዩኒቱ አባላት የሀገርን አደራ ተቀብለው ማንኛውንም ችግሮች በጽናት በመቋቋም ወንድም ለሆነው ጎረቤት ሀገር ሠላም እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነው።

የሄሊኮፕተር ዩኒት አዛዥ ሌተና ኮሎኔል ተሾመ ባጫ በበኩላቸው፤ የዩኒቱ አመራርና አባላት የነበራቸውን ሙያዊ ልምድ በመጠቀም ህዝብና መንግሥት የሰጧቸውን አደራ ከግብ ለማድረስ ሌት ተቀን በመረባረብ የሀገራችንን የአቪዬሽን አቅም ወደ ተግባር በመለወጥ የሠላም ማስከበር ግዳጆቻችንን በላቀ ብቃት በመፈጸም ለዛሬው የሜዳሊያ ቀን ደርሰናል። ማለታቸውን የዩኒቱ ሪፖርተር ማስተር ቴክኒሽያን ፍቃዱ አሸቱ ከስፍራው ያደረሰን ዘገባ ያመለከታል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
ኢንተርፕራይዙ ለከፍተኛ የሰራዊት እና ሲቭል አመራሮች ለስድስት ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...