ሞተራይዝድ ሻለቃው ስኬታማ ተልዕኮ እየፈጸመ መሆኑ ተገለፀ

 

በደቡብ ሱዳን ቦርደር ተሰማርቶ የሚገኘው የኢትዮጵያ 9ኛ የሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ውጤታማ ሥራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የ9ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፀጋዬ ገ/እግዚአብሄር እንደገለጹት፤ ሠራዊቱ ለሠላም ማስከበር ግዳጁ አፈፃፀም የወሰደውን ሥልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ግዳጁን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ የረጅም እና የአጭር ርቀት ቅኝት እንዲሁም የአውሮፕላን ቅኝት የሚያደርጋቸው ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም የሻለቃው አባል ግዳጁን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የ9ኛ ሻለቃ 2ኛ ሻምበል ዋና አዛዥ ሻለቃ ጨርቆስ ገ/ህይወት በበኩላቸው ሻምበሉ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ ሲሆን ኤርፖርት ጥበቃ፣ ተነቃናቂ እና ከሌሎች ሻምበሎች ጋር በመሆን የተለያዩ ግዳጆችን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!