ማዕከሉ የምስረታ በዓሉን አከበረ

 

በብሪትሽ ካውንስል የሰሜን ዕዝ ሠላም ማስከበር ቋንቋ ማሠልጠኛ ማዕከል የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት በደማቅ ሁኔታ አከበረ።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው በዕዙ የተዘጋጀውን ስጦታ በማበርከት ንግግር ያደረጉት የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ናቸው።

ጄኔራል መኮንኑ በዕለቱ እንደተናገሩት፤ የብሪትሽ ካውንስል የቋንቋ ማሠልጠኛ ማዕከል በዕዙ የ10 ዓመት ቆይታ ከ1ሺህ 150 የሆኑ የዕዙን አመራሮች አሰልጥኖ በማበቃት የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀው  በተገኘው ክህሎት በሠላም ማስከበር ተልዕኳችን ላይ ከፍተኛ የለውጥ ሂደት መመዝገቡን ጠቁመዋል።

የብሪትሽ መከላከያ አታሼ ኮሎኔል ማት ሙኑሮ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ ባለው የሠላም ማስከበር ስምሪቶች የሚሰጡትን ተልዕኮዎች ሁሉ በብቃት በመፈጸም ቀዳሚ የሆነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የቋንቋ ክህሎቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የብሪታኒያ መንግሥት አስፈላጊውን በጀት በመመደብ ፕሮጀክቱን እንደሚያስቀጥል ተናግረዋል።

የብሪትሽ ካውንስል አማካሪ ሚስተር ተር ሃር ባደረጉት ንግግር፤ የብሪታኒያ መንግሥት የሠላም ማስከበር ቋንቋ ማሠልጠኛ ማዕከላትን ከከፈተባቸው 40 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ጠቅሰው፤ ባለፉት 10 ዓመታት ከ12 በላይ ቅርንጫፎችን በመክፈት በቋንቋ ክህሎታቸው የተካኑ ብቁ አመራሮችን በማፍራት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ምንም ዓይነት ተዛማጅ መረጃ አልተገኘም!
በብዛት የተነበቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስተር ለልዩ ልዩ ሞያዎች ለሚመለመሉ የመመልመያ መስፈርት አወጣ
 
ማሳሰቢያ
ማሳሰቢያ
የመከላከያ ኢን/ህ/ግ/ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት መግለጫ (የአንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የተሳሳቱ መግለጫዎችን በተመለከተ)
Video poster
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ድርጅት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
ኢንተርፕራይዙ ለከፍተኛ የሰራዊት እና ሲቭል አመራሮች ለስድስት ተከታታይ ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ
የአለም አቀፍ ሰላም ማሰከብር ስልጠና ተሰጠ ከተለያዪ የኣፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ የሠራዊት አባላት ከጃፓን መንግስትጋር በመተባበር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አለም አቀፍ ሰላም...